Shukren
Abel Mulugeta
4:48ያሉትን ይበሉ ፍቅሯ ከረታኝ የወደደ ሟች ነው ይሄ መች ጠፋኝ የልቤን ካገኘሁ ከተሳካልኝ ለሚያልፍ አሉባልታ እኔስ ግድ የለኝ ባልዋልኩበት ውዬ ስሜ እንኳ ቢጠፋ ቃልኪዳን አለብኝ ፍቅርሽን ላልገፋ ቢወራ ቢነገር በድፍን ከተማ እኔስ ማንንም አልሰማ (ማንንም አልሰማ) ከላይ ሳይታደል በይሆናል ብቻ ሰው እንደፍቃዱ አያገኝም አቻ ይህን መሳይ ፍቅር ለኔ ካለውማ እኔስ ማንንም አልሰማ (ማንንም አልሰማ) ከዘሯ አይደለም ጉዳዬ መታመን ብቻ ነው እዳዬ ከገባው ፍቅር ስሙ አይኮራም በዘር በደሙ ከየት ትሁን ከየት ግድ የለኝም የሷ ዘር ፍቅር አይሆነኝም ካማረኝ እሷን ካልኩማ አልሻም ምክርም አልሰማ አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም ያሉትን ይበሉ ፍቅሯ ከረታኝ የወደደ ሟች ነው ይሄ መች ጠፋኝ የልቤን ካገኘሁ ከተሳካልኝ ለሚያልፍ አሉባልታ እኔስ ግድ የለኝ ከምእራብ ከደቡብ ከሰሜን ምስራቅ በዘር መሞሻሸር እኔ እንደው አላውቅ ካልተጠራጠራት ልቤ ካመነማ እኔስ ማንንም አልሰማ (ማንንም አልሰማ) ልጅ አድጎ ይለያል ከ'ናቱ ካ'ባቱ ሊጣምመር በፍቅር ከወደዳት ሚስቱ ደምሮ ቀንሶ ሀቁን ካገኘማ ልቤስ ማንንም አይሰማ (ማንንም አልሰማ) ከዘሯ አይደለም ጉዳዬ መታመን ብቻ ነው እዳዬ ከገባው ፍቅር ስሙ አይኮራም በዘር በደሙ ከየት ትሁን ከየት ግድ የለኝም የሷ ዘር ፍቅር አይሆነኝም ካማረኝ እሷን ካልኩማ አልሻም ምክርም አልሰማ አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም አልሰማም