Yeraralegne
Addisalem Assefa
6:39ማዕበሉ ፡ ለምን ፡ ገፋኝ ፡ አልልም ፡ ይግፋኝ ወጀቡ ፡ ለምን ፡ ነካኝ ፡ አልልም ፡ ይንካኝ አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ ሁሉን ፡ ይችላል ፡ በእኔ ፡ ላይ የነፍሴ ፡ ጌታ ፡ አይደለም ፡ ወይ ይችላል ፡ በእኔ ፡ ላይ ድንጋዩን ፡ ሁሉ ፡ እንቅፋቱን ከፊቴ ፡ ጠርጐ ፡ ተራራውን በእኔ ፡ ችሎ ፡ የማልችለውን አለማምዶኛል ፡ ተዐምራቱን ማቆም ፡ ይችላል ፡ ማዕበሉን ማዘዝ ፡ ይችላል ፡ ንፋሳቱን ባያቆመውም ፡ አውራቂሱን እሻገራለሁ ፡ ይዤ ፡ ቃሉን ቁዘማውን ፡ ይውሰደው እርሱ ፡ የጠላቴ ፡ ንብረት ፡ ነው ሞት ፡ አይሆንም ፡ በሕይወቴ ገልብጦታል ፡ መድሃኒቴ አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ የሚሆንለት ፡ እርሱ ፡ እንዳለው የሚቆምለት ፡ እንዳሰበው የዕድሜህን ፡ ቁጥር ፡ የሚያሰላው የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ የእኔም ፡ ነው ስለዚህ ፡ ለምን ፡ ሽንፈትን ፡ ላውራ ለትንሽ ፡ ነገር ፡ እንደተጠራ ልታመን ፡ እንጂ ፡ ኃይል ፡ ባለው ስሙ ፡ እግዚአብሔር ፡ በተባለው ቁዘማውን ፡ ይውሰደው እርሱ ፡ የጠላቴ ፡ ንብረት ፡ ነው ሞት ፡ አይሆንም ፡ በሕይወቴ ገልብጦታል ፡ መድሃኒቴ አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ ኦሮምኛ አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ