Zarem Yiwodegnal
Azeb Hailu
6:25አዝ፦ እልፍ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ ፡ አሃሃ እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ አረገኝ ፡ ማዳኑ ፡ ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ ፡ ኦሆሆ ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ ፡ አሃሃ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ አሰራሩን ፡ ያዩ ፡ ሁሉ ፡ እንዲደነቁ ፡ ኦሆሆ ሁሉ ፡ እንዲደነቁ ከልምምድ ፡ ውጪ ፡ ከተዘወተረው አዲስ ፡ ነገር ፡ መስራት ፡ ልማዱ ፡ የሆነው በውኃ ፡ ላይ ፡ እንድሄድ ፡ እንድቆም ፡ አዘዘኝ ቃል ላከልኝና፡ አትፍሪ ፡ ነይ ፡ አለኝ ውኃ ፡ ላይ ፡ በታንኳ ፡ ሁሌ ፡ ከመንሳፈፍ ኢሄም ፡ አለ ፡ ብሎ ፡ አደረገኝ ፡ እልፍ ከታንኳ ፡ ያልወረዱ ፡ ቢሉም ፡ ምትሃት ፡ ነው ለካስ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ውኃም ፡ መንገዱ ፡ ነው አዝ፦ እልፍ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ ፡ አሃሃ እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ አረገኝ ፡ ማዳኑ ፡ ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ ፡ ኦሆሆ ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ ፡ አሃሃ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ አሰራሩን ፡ ያዩ ፡ ሁሉ ፡ እንዲደነቁ ፡ ኦሆሆ ሁሉ ፡ እንዲደነቁ እንሂድ ፡ ወዲያማዶ ፡ እንሂድ ፡ እንሻገር ሥሙም ፡ ጌርጌስኖን ፡ ወደሚባል ፡ አገር ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ብዙ ፡ የተቸገረ በመቃብር ፡ ስፍራ ፡ አለና ፡ የታሰረ እልፍ ፡ እንበልና ፡ የታሰረ ፡ ይፈታል ብሎ ፡ ሲያሻግረን ፡ ይሄ ፡ ቸሩ ፡ ጌታ በስፍራው ፡ ስንደርስ ፡ ይህ ፡ ሰው ፡ ተፈወሰ ጌታም ፡ ተገናኘው ፡ ልቡም፡ ተመለሰ አዝ፦ እልፍ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ ፡ አሃሃ እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ አረገኝ ፡ ማዳኑ ፡ ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ ፡ ኦሆሆ ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ ፡ አሃሃ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ አሰራሩን ፡ ያዩ ፡ ሁሉ ፡ እንዲደነቁ ፡ ኦሆሆ ሁሉ ፡ እንዲደነቁ ሌሊቱን ፡ በሙሉ ፡ ስደክም ፡ ፍለጋ መረቤም ፡ አንድ ፡ ዓሣ ፡ ሳይዝልኝ ፡ ነጋ የጌታን ፡ ቃል ፡ ይዤ ፡ ስጥል ፡ ወደ ፡ ጥልቁ ታንኳዬን ፡ ዓሣዎች ፡ ሞልተው ፡ አስጨነቁ መሄድ ፡ እንደቃሉ ፡ ፈቀቅ ፡ ማለት በውስጡ ፡ አለና ፡ ብዙ ፡ በረከት ገፍቶ ፡ አስጠግቶኝ ፡ አድርጐኝ ፡ እልፍ በመንፈሱ ፡ ሙላት ፡ ሆነ ፡ መንሳፈፍ አዝ፦ እልፍ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ ፡ አሃሃ እልፍ ፡ ወደ ፡ ማዶ አረገኝ ፡ ማዳኑ ፡ ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ ፡ ኦሆሆ ሊያሳየኝ ፡ አቅዶ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ ፡ አሃሃ ፈቀቅ ፡ ወደ ፡ ጥልቁ አሰራሩን ፡ ያዩ ፡ ሁሉ ፡ እንዲደነቁ ፡ ኦሆሆ ሁሉ ፡ እንዲደነቁ