Notice: file_put_contents(): Write of 638 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Betty Tezera - Edmeye Betih Yilek | Скачать MP3 бесплатно
Edmeye Betih Yilek

Edmeye Betih Yilek

Betty Tezera

Длительность: 5:45
Год: 2022
Скачать MP3

Текст песни

የተወደደ ጥበብ የሞላው
ክብር ሲሆንልት ዝና ሲተርፈው
የአባቶቹን አምላክ እንደማያውቀው
ጣዖት አምልኮ ሞት ሆነ ፍጻሜው

አዝ፦ ዕድሜዬ ይለቅልኝ ቤትህ
ይለቅልኝ በፊትህ
ሕይወቴ ይመርልኝ ፊትህ
ይመርልኝ በፊትህ

ሩጫዬ እንዳይገታ
ጠብቀኛ የእኔ ጌታ
እኔ እንዳልሆን ለእኔው ጠላቴ
ሰውረኝ ከዓይን አምሮቴ

አህያ ፍለጋ ተልኮ ቢወጣ
እጣ ወደቀበት ህዝብን እንዲመራ
ከፍልስጤማዊ ነጻ እንዲያወጣ

ደርሶ ንጉሥ ሲሆን ትህትና አጣ
ክፉ መንፈስ ያዘው ከአንተ መንገድ ወጣ
መውደቂያው ሆነበት የልቡ ተራራ

አዝ፦ ዘመኔ ይለቅልኝ ቤትህ
ይለቅልኝ በፊትህ
ሕይወቴ ይመርልኝ ፊትህ
ይመርልኝ በፊትህ

ሩጫዬ እንዳይገታ
ጠብቀኛ የእኔ ጌታ
እኔ እንዳልሆን ለእኔው ጠላቴ
ሰውረኝ ከዓይን አምሮቴ

በትንሳኤው ጉልበት ዓይናቸው የበራ
ጨከኑ በሕይወት ለሰሙት አደራ
ቤታቸውን ሰጡ ለወንጌል አደራ

አርበኞች ሆነዋል እስሩም ቢጠና
ነገሥታት ፊት ቆሙ ወንጌልን ሰበኩና
ሳማአት ሆነው አለፉ ዋጋ ተመኑና

ድል ለነሳው ከሕይወት አክሊል ታዘዳጃለህ
ድል ለነሳው በቤትህ እንዲኖር ትሾመዋለህ
ጅማሬዬ እንዳማረልኝ ፍጻሜዬም ይስመርልኝ
መዝገብ ላከማች በሠማይ ቤትህ
ብል በማይበላው በሌለበት

ስታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ
ዕድሜዬ ይልቅ እቤትህ
ስታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ
ዘመኔ ይልቅ እቤትህ

ድል ለነሳው ከሕይወት አክሊል ታገዳጃለህ
ድል ለነሳው በቤትህ እንዲኖር ትሾመዋለህ
ጅማሬዬ እንዳማረልኝ ፍጻሜዬም ይስመርልኝ
መዝገብ ላከማች በሠማይ ቤትህ
ብል በማይበላው በሌለበት

ስታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ
ዕድሜዬ ይልቅ እቤትህ
ስታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ
ዘመኔ ይልቅ እቤትህ
ስታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ
ሕይወቴ ይመር እፊትህ

ስታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ
ወበቴ ይልቅ እቤትህ
ስታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ
ዕድሜዬ ይልቅ እቤትህ
ስታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ
ዘመኔ ይልቅ እቤትህ