Alresawem
Daniel Amdemichael
4:41የሚያስጨንቀኝን ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጣልኩና ዝማሬን ፡ ዘመርኩኝ ፡ በገና ፡ ያዝኩና አንተ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ብዬ ፡ የልቤን ፡ ብነግረው እግዚአብሔር ፡ መንገዴን ፡ መልካም ፡ አደረገው (፪x) ማነው ፡ ተጨንቆ ፡ ሽቅብ ፡ ያደገ የእራሱን ፡ ጸጉር ፡ ነጭ ፡ ያደረገ ዛሬ ፡ በሆነው ፡ ነፍሴ ፡ አመስግኜው ነገን ፡ አላውቅም ፡ ነገ ፡ የእርሱ ፡ ነው የዘለዓለሙ ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም ፡ ያዳነኝ በዚህም ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እንዲያውቃል ፡ እንዲያኖረኝ የሚያስጨንቀኝን ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጣልኩና ዝማሬን ፡ ዘመርኩኝ ፡ በገና ፡ ያዝኩና አንተ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ብዬ ፡ የልቤን ፡ ብነግረው እግዚአብሔር ፡ መንገዴን ፡ መልካም ፡ አደረገው (፪x) ምግብን ፡ ከሰጠ ፡ ለሠማይ ፡ ወፎች አምላክ ፡ ካሰበ ፡ ለምድር ፡ አበቦች ለሰራኝማ ፡ ፈጥሮ ፡ በአምሳሉ ተአምራት ፡ አለው ፡ ልቁም ፡ በቃሉ ሃሳቤን ፡ በእርሱ ፡ ጥዬ ፡ እምነቴን ፡ ላጠንክረው በኢየሱስ ፡ በጌታዬ ፡ ልቤን ፡ ላሳርፈው የሚያስጨንቀኝን ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጣልኩና ዝማሬን ፡ ዘመርኩኝ ፡ በገና ፡ ያዝኩና አንተ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ብዬ ፡ የልቤን ፡ ብነግረው እግዚአብሔር ፡ መንገዴን ፡ መልካም ፡ አደረገው (፪x) እርሱ ፡ ስለእኔ ፡ ያስባል ፡ ያለ በጌታ ፡ ታምኖ ፡ ሸክሙን ፡ የጣለ ማይነቃነቅ ፡ መሰረት ፡ ያለው የጊዜው ፡ ወጀብ ፡ ያላናወጠው ተመስገን ፡ ንገሥ ፡ ይላል ፡ በኢየሱስ ፡ ልቡ ፡ ያረፈ ሁልጊዜ ፡ በአምላኩ ፡ ላይ ፡ እየተደገፈ የሚያስጨንቀኝን ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጣልኩና ዝማሬን ፡ ዘመርኩኝ ፡ በገና ፡ ያዝኩና አንተ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ብዬ ፡ የልቤን ፡ ብነግረው እግዚአብሔር ፡ መንገዴን ፡ መልካም ፡ አደረገው (፪x)