Amesegnalehu
Daniel Amdemichael
8:06አዝ፦ ይገርመኛል ፡ የአምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ቸርነቱን አልታክትም ፡ ሁሌ ፡ ባወራው ፡ ምህረቱን እርሱ ፡ በሰራው ፡ ጸድቅ ፡ እኔን ፡ ያኖረኛል ስለመዳኔ ፡ ላከብረው ፡ ይገባኛል ፡ ኦሆ ላመስግነው ፡ ከፍ ፡ ላድርገው ፡ ክብርን ፡ ልስጠው ፡ ኦሆ በሠማዩ ፡ መዝገብ ፡ ስሜን ፡ ስለጻፈው ደስ ፡ ይለኛል ፡ ጸድቄአለሁኝ ፡ በእርሱ ፡ ስራ ፡ ኦሆ እኖራለሁ ፡ ድንቁን ፡ ታሪኩን ፡ ሳወራ ኢየሱስ ፡ መድኅኔ ፡ ማረፊያ ፡ ሆኖኛል ከሞት ፡ ከጨለማ ፡ መንጥቆ ፡ አውጥቶኛል የከበረ ፡ ስሙን ፡ ዘወትር ፡ እየጠራሁ ፡ ቅኔን ፡ እቀኛለሁ በታላቅ ፡ ጉባኤ ፡ በልጆቹ ፡ መሃል ፡ አመሰግናለሁ በልጆቹ ፡ መሃል ፡ አመሰግናለሁ (፫x) ፡ አመሰግናለሁ ተመስገን ፡ ትላለች ፡ እርሱ ፡ ያዳናት ፡ ነፍሴ ሳመልከው ፡ ደስ ፡ አለኝ ፡ በእውነት ፡ በመንፈሴ አድናቆቴም ፡ ይኸው ፡ አክብሮቴም ፡ ይኸው ፡ ፊቱ ፡ ልስገድለት ለጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ ለነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ ሞገስ ፡ ይሁንለት ለጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ ሞገስ ፡ ይሁንለት ፡ ሞገስ ፡ ይሁንለት ለነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ ለጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ ሞገስ ፡ ይሁንለት አዝ፦ ይገርመኛል ፡ የአምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ቸርነቱን አልታክትም ፡ ሁሌ ፡ ባወራው ፡ ምህረቱን እርሱ ፡ በሰራው ፡ ጸድቅ ፡ እኔን ፡ ያኖረኛል ስለመዳኔ ፡ ላከብረው ፡ ይገባኛል ፡ ኦሆ ላመስግነው ፡ ከፍ ፡ ላድርገው ፡ ክብርን ፡ ልስጠው ፡ ኦሆ በሠማዩ ፡ መዝገብ ፡ ስሜን ፡ ስለጻፈው ደስ ፡ ይለኛል ፡ ጸድቄአለሁኝ ፡ በእርሱ ፡ ስራ ፡ ኦሆ እኖራለሁ ፡ ድንቁን ፡ ታሪኩን ፡ ሳወራ አምላክ ፡ አባት ፡ ሆነኝ ፡ በወንጌል ፡ አምኜ በደሙ ፡ ዋጋ ፡ ገዛኝ ፡ እንድኖር ፡ ልጁ ፡ ሆኜ እንግዲህ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ስለታላቅ ፡ ፍቅሩ ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ ልናገር ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ መዳኔን ፡ እያሰብኩ ፡ ከማመስገን ፡ በቀር ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ መዳኔን ፡ እያሰብኩ ፡ ከማመስገን ፡ በቀር (፪x)