Bayew Bayew
Dawit Tsige
5:05አስችሎሽ ይሆን አስችሎሽ? በእኔ ላይ ሌላ ሰው የሆንሽ አስችሎሽ ይሆን አስችሎሽ? በእኔ ላይ ሌላ ሰው የሆንሽ አስችሎሽ ይሆን አስችሎሽ? በእኔ ላይ ሌላ ሰው የሆንሽ (አሃ) እኔ እንጃ እኔ እንጃ እኔ እንጃልኝ እኔ እንጃ እኔ እንጃ እኔ እንጃልኝ ፍቅርሽ ባይኔ ላይ ዞረብኝ እኔ እንጃ እኔ እንጃ እኔ እንጃልኝ ፍቅርሽ ባይኔ ላይ ዞረብኝ ኧረ እኔስ እንጃ እኔ እንጃልኝ አድረን ስንውል ስንኖር አንድ ላይ (እምምም) አንቺ ብቻ ነበርሽ የኔ ነፍስ የበላይ (አይጣል) መሄድ ለማሰብሽ ጥርጥር ሳይገባኝ (እምምም) ሳላውቅሽ መኖሬ እያደር አስከፋኝ (አይጣል) እያሰብኩሽ ጠፋሽ እያመንኩሽ ከፋሽ ከታየሽ ግን ላንቺ አለም ሞልታ ትስፋሽ ተ—ይ ተይ ተይ ተይ ተ—ይ ተይ ተይ ተይ ተይ ቀኑም አይባስ ተይ ቀኑም አይሄድ ተይ ስለፍቅር ተይ ስለመውደድ ሚሻል ሲገኝ ምን ያስከፋል? ያንቺ ደስታ ለእኔ ይተርፋል ባሳለፍነው ህይወታችን ማደግ ነበር ምኞታችን ይገኝ እንጂ መልካም እድል ለአንዱ ሞልቶ ለአንዱ አይጎድል እኔም እኮ አለኝ ድርሻ ሲያምር ያንቺ መጨረሻ አስችሎሽ ይሆን አስችሎሽ? በእኔ ላይ ሌላ ሰው የሆንሽ አስችሎሽ ይሆን አስችሎሽ? በእኔ ላይ ሌላ ሰው የሆንሽ አስችሎሽ ይሆን አስችሎሽ? በእኔ ላይ ሌላ ሰው የሆንሽ እኔ እንጃ እኔ እንጃ እኔ እንጃልኝ እኔ እንጃ እኔ እንጃ እኔ እንጃልኝ ፍቅርሽ ባይኔ ላይ ዞረብኝ እኔ እንጃ እኔ እንጃ እኔ እንጃልኝ ፍቅርሽ ባይኔ ላይ ዞረብኝ ኧረ እኔስ እንጃ እኔ እንጃልኝ አንቺን ካስመለጠኝ ወረት ከእጄ መዳፍ (እምምም) ፍቅርሽን ልርሳ ብል መች ሊቀለኝ እንደ አፍ (አይጣል) ዛሬ ብጠፊብኝ አርገሽኝ ብቸኛ (እምምም) እንግዲህ ለነገው ከየት ላግኝ መፅናኛ (አይጣል) እያሰብኩሽ ጠፋሽ እያመንኩሽ ከፋሽ ከታየሽ ግን ላንቺ አለም ሞልታ ትስፋሽ ተ—ይ ተይ ተይ ተይ ተ—ይ ተይ ተይ ተይ ተይ ቀኑም አይባስ ተይ ቀኑም አይሄድ ተይ ስለፍቅር ተይ ስለመውደድ ሚሻል ሲገኝ ምን ያስከፋል? ያንቺ ደስታ ለእኔ ይተርፋል ባሳለፍነው ህይወታችን ማደግ ነበር ምኞታችን ይገኝ እንጂ መልካም እድል ለአንዱ ሞልቶ ለአንዱ አይጎድል! እኔም እኮ አለኝ ድርሻ ሲያምር ያንቺ መጨረሻ እኔ እንጃ እኔ እንጃ እኔ እንጃልኝ እኔ እንጃ እኔ እንጃ እኔ እንጃልኝ ፍቅርሽ ባይኔ ላይ ዞረብኝ እኔ እንጃ እኔ እንጃ እኔ እንጃልኝ ፍቅርሽ ባይኔ ላይ ዞረብኝ ኧረ እኔስ እንጃ እኔ እንጃልኝ