Yewollo Lij

Yewollo Lij

Dereje Degefaw

Альбом: Alkerm
Длительность: 6:54
Год: 2022
Скачать MP3

Текст песни

አለም ሸጋዬ ሆይ እንዴት ነሽ
እንዴት ነሽ
አንቺ ሸጋ ጉብል እንዴት ነሽ
እንዴት ነሽ
አለም ሸጋዬ ሆይ እንዴት ነሽ
እንዴት ነሽ

ይቺ የወሎ ልጅ አንገተ ዥጉርጉር
ይቺ የአምባሰል ልጅ አንገተ ዥጉርጉር
መንገዱን አስላ ሰደደችኝ በዱር
መንገዱን አስላ ሰዳኛለች በዱር
ወሎ መሄዴ ነው እኔስ ለሽርሽር
ከቆንጆዎች ጋራ እያልኩኝ ያዝ አብሽር

ኧረ ዘመድዬ ኧረ ዘመድዬ ኧረ ዘመድዬ
እንጃ እንጃ አንቺዬ

ከመከም አለችኝ እንደምን ልከምከም
ሀኪሜም እሷው ናት አምጡልኝ ልታከም
እስክስታ አወራረድ አይችልም ጉልበቴ
እንደው መታ መታ መላው ሰውነቴ
ነይ ሰውነቴ ነይ ነይ
ነይ ሰውነቴ ነይ ነይ

አለም ሸጋዬ ሆይ እንዴት ነሽ
እንዴት ነሽ
አንቺ ሸጋ ጉብል እንዴት ነሽ
እንዴት ነሽ
አለም ሸጋዬ ሆይ እንዴት ነሽ
እንዴት ነሽ

የባህል ቀሚሱን ድሪውን አርገሻል
ፀጉርሽን ሹርባ አሰርተውሻል
አንገትሽን በሾህ አስነቅሰውታል
ጣትሽን በእንሶስላ አሳምረውታል
ይህ ሁሉ መኳኳል ምን ያደርግልሻል
ወሎዬ ነኝ ብትይ ስሙ ይበቃሻል

ኧረ ዘመድዬ ኧረ ዘመድዬ ኧረ ዘመድዬ
እንጃ እንጃ አንቺዬ

ከመከም አለችኝ እንደምን ልከምከም
ሀኪሜም እሷው ናት አምጡልኝ ልታከም
እስክስታ አወራረድ አይችልም ጉልበቴ
እንደው መታ መታ መላው ሰውነቴ
ነይ ሰውነቴ ነይ ነይ
ነይ ሰውነቴ ነይ ነይ

እጥፍ ዘርጋ እያለች የልቤን ሰላይ
መጣች የወሎ ልጅ በገራዶ ላይ
በወልድያ በኩል እያለች ዘው ዘው
መጣች አንዱን ልቤን ልትወሰውሰው
በአምባሰል ዙረሽ
በእመቤቴ ማርያም ለነፍሴ ድረሽ

ኧረ ዘመድዬ ኧረ ዘመድዬ ኧረ ዘመድዬ
እንጃ እንጃ አንቺዬ

ከመከም አለችኝ እንደምን ልከምከም
ሀኪሜም እሷው ናት አምጡልኝ ልታከም
እስክስታ አወራረድ አይችልም ጉልበቴ
እንደው መታ መታ መላው ሰውነቴ
ነይ ሰውነቴ ነይ ነይ
ነይ ሰውነቴ ነይ ነይ