Notice: file_put_contents(): Write of 668 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Ephrem Tamiru - Salasbew | Скачать MP3 бесплатно
Salasbew

Salasbew

Ephrem Tamiru

Длительность: 7:10
Год: 2006
Скачать MP3

Текст песни

ሳላስበዉ ለካ አፍቅሬሻለዉ
አንቺን ሳስብ ቀኑን ዉዬ አድራለዉ
የኔ እንደማትሆኚ በእርግጥ አዉቀዋለዉ በእርግጥ አዉቃለዉ
ያዘዘኝ ልቤ ነዉ እንዴት አደርጋለዉ እንዴት አደርጋለዉ

ሳላስበዉ ለካ አፍቅሬሻለዉ
አንቺን ሳስብ ቀኑን ዉዬ አድራለዉ
የኔ እንደማትሆኚ በእርግጥ አዉቀዋለዉ በእርግጥ አዉቃለዉ
ያዘዘኝ ልቤ ነዉ እንዴት አደርጋለዉ እንዴት አደርጋለዉ

የማይሽር ፍቅርሽ አሄሄ በልቤ ተክለሽ
በሬን ዘጋግቼ እህህ እያልኩኝ ታድያ እንዴት ነሽ
ስጨነቅ አድራለሁ አሄሄ በሀሳብ ስዋትት
እንዴት አበሳ ነዉ የማያኙትን ሰዉ መመኘት
እንዴት አበሳ ነዉ የማያኙትን ሰዉ መመኘት

የፍቅር አምላክ ልፋ ቢለኝ ልፋ ቢለኝ ድከም ቢለኝ
የማልችለዉን ሀያል ፍቅርሽን አሸከመኝ አሸከመኝ
እንደዉ በሀሳብ ትዝ እያልሽኝ አታባብይኝ አታባብይኝ
እኔም ለራሴ አንቺን ተርቤ የከፋኝ ነኝ
የከፋኝ ነኝ ሆድ የባሰዉ የከፋኝ ነኝ ሆድ የባሰዉ

ኦሆ እርሜን በፍቅር ኦሆ ልቤን ሰጥቼ አሄ ልቤን ሰጥቼ
ኦሆ እንዲያዉ በምኞት ኦሆ ቀረሁ ጓጉቼ አሄ ቀረሁ ጓጉቼ
ኦሆ እርሜን በፍቅር ኦሆ ልቤን ሰጥቼ ኦሆ ልቤን ሰጥቼ
ኦሆ እንዲያዉ በምኞት ኦሆ ቀረሁ ጓጉቼ አሄ አንቺን አጥቼ

ሳላስበዉ ለካ አፍቅሬሻለዉ
አንቺን ሳስብ ቀኑን ዉዬ አድራለዉ
የኔ እንደማትሆኚ በእርግጥ አዉቀዋለዉ በእርግጥ አዉቃለዉ
ያዘዘኝ ልቤ ነዉ እንዴት አደርጋለዉ እንዴት አደርጋለዉ

ሳላስበዉ ለካ አፍቅሬሻለዉ
አንቺን ሳስብ ቀኑን ዉዬ አድራለዉ
የኔ እንደማትሆኚ በእርግጥ አዉቀዋለዉ በእርግጥ አዉቃለዉ
ያዘዘኝ ልቤ ነዉ እንዴት አደርጋለዉ እንዴት አደርጋለዉ

በአካል ተዋህደን አሄሄ መኖራችን ቢቀር
ምንም ነገር ቢሆን አያግደኝም አንቺን ከማፍቀር
ቃሌን አላጥፈዉም አሄሄ በህይወት እስካለዉ
በአንቺ ሚመጣዉን ችግር አብሬ እሸፋፍናለዉ
በአንቺ ሚመጣዉን ችግር አብሬ እሸፋፍናለዉ

የዉስጤን ሀሳብ እወቂልኝ ሁሌም ስሜቴን ተረጂልኝ
ከጄ ባትገቢም የኔም ባትሆኚም እስከ ዘላለም አፍቃሪሽ ነኝ
ከማንም በላይ የማስብሽ የማቀርብሽ አንቺ ነበርሽ
ምን ይደረጋል አንዳች አላልኩሽ ልቀርነ ነዉ
ልቀርነ ነዉ እንዲዉ ሳላገኝሽ ልቀርነ ነዉ እንዲዉ ሳላገኝሽ

ኦሆ እርሜን በፍቅር ኦሆ ልቤን ሰጥቼ አሄ ልቤን ሰጥቼ
ኦሆ እንዲያዉ በምኞት ኦሆ ቀረሁ ጓጉቼ አሄ ቀረሁ ጓጉቼ

የዉስጤን ሀሳብ እወቂልኝ ሁሌም ስሜቴን ተረጂልኝ
ከጄ ባትገቢ የኔም ባትሆኚም እስከ ዘላለም አፍቃሪሽ ነኝ
ከማንም በላይ የማስብሽ የማቀርብሽ አንቺ ነበርሽ
ምን ይደረጋል አንዳች አላልኩሽ ልቀርነ ነዉ እንዲዉ ልቀርነ ነዉ እንዲዉ

የዉስጤን ሀሳብ እወቂልኝ ሁሌም ስሜቴን ተረጂልኝ
ከጄ ባትገቢም የኔም ባትሆኚም እስከ ዘላለም አፍቃሪሽ ነኝ
ከማንም በላይ የማስብሽ የማቀርብሽ አንቺ ነበርሽ
ምን ይደረጋል አንዳች አላልኩሽ ልቀርነ ነዉ እንዲዉ ልቀርነ ነዉ እንዲዉ