Semu
Ezira Hailemichel
5:22በልቤ ከተማ ተመላለስበት ይረጋል ሕይወቴ አንተ ስታልፍበት ወደልፍኜ ግባ እረፍ በምንጣፌ እንዳመልክህ ጌታ እንባዬን አርግፌ(2) ባለፀጋ ስትሆን ድሆች ከበውሃል ለንግስና ዙፋን አህያን መርጠሃል አጀብ አትፈልግም አውቃለሁ ጌታ ብቻህን ነበረ ደጄን ስትመታ ለጠላቴ አሰራር ዋሻ የሆንኩትን ስራኝ እንደ ገና ቤተ መቅደስህን በልቤ ከተማ ተመላለስበት ይረጋል ሕይወቴ አንተ ስታልፍበት ወደልፍኜ ግባ እረፍ በምንጣፌ እንዳመልክህ ጌታ እንባዬን አርግፌ(2) ድንግዝግዝ ኑሮዬ በምራቅህ ይብራ ጨለማ አይዝህም አንተ ስትሰራ ማረኝ ያለህ እጆች ሲያሸበሽቡልህ ሰምቼ አልቀረሁም በብርሃን አየሁህ ለጠላቴ አሰራር ዋሻ የሆንኩትን ስራኝ እንደ ገና ቤተ መቅደስህን በልቤ ከተማ ተመላለስበት ይረጋል ሕይወቴ አንተ ስታልፍበት ወደልፍኜ ግባ እረፍ በምንጣፌ እንዳመልክህ ጌታ እንባዬን አርግፌ(2) ከያዕቆብ ጉድጓድ ብቀዳም አብዝቼ ዛሬም በጥማት ነኝ ከቶ መች ረክቼ የህይወት ውሃ ምንጭ ነፍስን የምትመልስ በበረሃው ልቤ ለዘላለም ፍሰስ ለጠላቴ አሰራር ዋሻ የሆንኩትን ስራኝ እንደ ገና ቤተ መቅደስህን