Zemen Yezema
Ezira Hailemichel
5:37ለክብርሽ አለኝ ምስጋና ከትውልድ አንዱ ነኝና ሳልታክት የምዘምረው ኪዳንሽ ስለረዳኝ ነው በሔዋን መተላለፍ መች ቀረው ምድረበዳ በልጅሽ ቤዛ መሆን አመለጥኩኝ ከፍዳ አልቀረም ከንቱ ሆኖ ነቢያት ትንቢታቸው ተፈጽሟል ድንግል ሆይ መሰላል ሆነሻቸው ለክብርሽ አለኝ ምስጋና ከትውልድ አንዱ ነኝና ሳልታክት የምዘምረው ኪዳንሽ ስለረዳኝ ነው የህይወት ውሃ ጠጣው ከማህጸንሽ መንጭቶ ከድካም አሳረፈኝ መዳፎቹን ዘርግቶ በላይ በሰማያት ጫፍ ለከበርሽው እናቴ ፀጋሽን ሊመሰክር ተፈቷል አንደበቴ ለክብርሽ አለኝ ምስጋና ከትውልድ አንዱ ነኝና ሳልታክት የምዘምረው ኪዳንሽ ስለረዳኝ ነው ወደ እኔ ስትመጪ ዘለልኩኝ በደስታ ነፍሴን በሃሴት ሞላው የአንደበትሽ ሰላምታ አንቺ ከእኔ ጋር ካለሽ በአንዳች አልሰጋም ቃል አለና በሆድሽ የሚሰጠኝ ሰላም ለክብርሽ አለኝ ምስጋና ከትውልድ አንዱ ነኝና ሳልታክት የምዘምረው ኪዳንሽ ስለረዳኝ ነው ማርያም ማርያም ስላልኩኝ አትሸበር ጠላቴ ገና ከፍ ያደርጋታል ዜማዬና ቅኝቴ በኤልሳቤት ውዳሴ በገብርኤል ሰላምታ አንደበቴን ሳልሰስት አከብራታለው ገና