Kalkidan
Hamelmal Abate
ሲያዝንና ሲደሰት ሲያፈቅርም ከልቡ ስሜቱን ይገልጻል በሞያ ጥበቡ ሲያዝንና ሲደሰት ሲያፈቅርም ከልቡ ስሜቱን ይገልጻል በሞያ ጥበቡ ሁሌም ለአዲስ ነገር ራሱን ያዘጋጀ ጥበበኛ አይምሮ ጥበብ ያደራጀ የህይወትን ዙሪያ ውስጡን ይዳሳል ብዙ እንቅፋት አለው ይወድቃል ይነሳል ውጥኑን ጀምሮት እስከሚጨርሰው ልረፍን አያውቅም ከግብ እስኪያደርሰው የሙያ ድግሱን በመድርክ አቅርቦ የታዳሚን መንፈስ አዝናንቶ መግቦ የጥረቱን ዋጋ የድካም ውጤቱ የህዝብ አድናቆት ነው የዘላለም ሀብቱ የህዝቡ ፍቅር እንጂ ሀብትና ንብረቱ ሌላ ምን ቅርስ አለው በቤት በማጀቱ እውነታው ይሄው ነው የከያኒ ውበቱ ሁል ግዜ ጠባቂ የወሩን መባቻ ደርሶም ኪሱ አይሞላ ያው ጠብታ ብቻ ሆዱን ለማሸነፍ ባይሸማቀቅም የጎጆ ሽንቁር የጎጆ ሽንቁሩን ደፍኖበት አያውቅም ላቡ ከፍሬው ጋር እስከሚሆን አቻ ደስተኛነቱ ነው የሚስጥሩ መፍቻ ላቡ ከፍሬው ጋር እስከሚሆን አቻ ደስተኛነቱ ነው የሚስጥሩ መፍቻ