Kalkidan
Hamelmal Abate
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ይመስገን ይመስገን ይመስገን ከዘመን ዘመን አሸጋግሮ አሮጌው በአዲስ ተቀይሮ ለዚ ያደረሰን ፈጣሪያችን ይክበር ይመስገን እለምን ሰላም ጤናዬን ነግሬው ነበረ የሆድ ሚስጥሬን የልቤ ደረሰ አዎን ደረሰ ጌታ ተመስገን ፀሎቴ ደረሰ አዎን ደረሰ አምላክ ተመስገን ኦሆሆይ የመከራዬ ቀንበር ተሰብሯል እህ የልቤ ሀዘን ባንተ ተቀብሯል እህ ዘመድ ሲርቀኝ የሆንከኝ ወገን አሄ ለዚ ያበቃኸኝ ክበር ተመስገን ክብር ጌታ ተመስገን ክብር አምላክ ተመስገን ክብር ጌታ ተመስገን ክብር አምላክ ተመስገን እንባዬንም ጠርጎ ሀዘኔን አርቆ አምላክ ነው የረዳኝ የኔን ጉዳት አውቆ የአለም መዳኒት ደጋፊና አለኝታ ልዘምር ለክብርህ ላረከው ውለታ ታምር ነው ያንተ ነገር ድንቅ ነው ያንተ ስራ ስጦታህ አይነገር ውለታህ አይወራ ታምር ነው ያንተ ነገር ድንቅ ነው ያንተ ስራ ወሮታህ አይከፈል ውለታህ አይወራ ኦሆ ጬኸቴን ሰምተህ ችላ ያላልከኝ እኽ ተድላና ደስታ ያደልከኝ አሀ ከዙፋንህ ላይ ያደላደልከኝ አኼን አምላኬ አንተ ነህ ከፍ ያደረከኝ ክብር ጌታ ተመስገን ክብር አምላክ ተመስገን ጌታ ሆይ ተመስገን ክብር አምላክ ተመስገን ድንቅ ተአምር አምላክ ያንተ ስራ ጭለማውን ገፈህ ፀሐይ የምታበራ ምስጋናና ክብር ላንተ እንዴት ያንስሀል ተመስገን አምላኬ ምን የከፈልሀል ታምር ነው ያንተ ነገር ድንቅ ነው ያንተ ስራ አለፍኩት ያን አቀበት ወጣውት ካንተጋራ ታምር ነው ያንተ ነገር ድንቅ ነው ያንተ ስራ አለፍኩት ያን አቀበት ወጣውት ካንተጋራ ታምር ነው ያንተ ነገር ድንቅ ነው ያንተ ስራ አለፍኩት ያን አቀበት ወጣውት ካንተጋራ ተመስገን ተመስገን ተመስገን (ተመስገን) ይመስገን ይመስገን ይመስገን (ይመስገን)