Emelalehu
Hayleyesus Feyssa
4:49ተይ በልባችን ሁሉን ነገር አምቀን ተይ ውሎ ሲያድር አንድ ቀን ተይ ብንጣላ የለም የሚያስታርቀን ተይ እንዳንቀር ተራርቀን ተይ በልባችን ሁሉን ነገር አምቀን ተይ ውሎ ሲያድር አንድ ቀን ተይ ብንጣላ የለም የሚያስታርቀን ተይ እንዳንቀር ተራርቀን ኩራት ክብሬ ስንል ነጋ ጠባ እንደተኮራረፍን ሳንግባባ ይቅርታ መጠየቅ መስሎን ሽንፈት አልህ ባንጋባስ ምን አለበት ውስጣችን እውነቱን እያወቀው ለይምሰል በአፋችን ብንደብቀው አንድ ቀን ተጣልተን ብንቀር መና የሚለን ሰው የለም አባከና ፍቅርና መቻቻል ባለበት ፈጣሪም ይሰጣል በረከት በህልህ ያለውን አፍርሰን መገንባት ይከብዳል መልሰን ተይ ተይ ተይ ረጋ ብለሽ አስቢ ተይ ይቅር ይቅር ይቅር ሰላም ይኑረን ተይ ተይ በልባችን ሁሉን ነገር አምቀን ተይ ውሎ ሲያድር አንድ ቀን ተይ ብንጣላ የለም የሚያስታርቀን ተይ እንዳንቀር ተራርቀን ተይ በልባችን ሁሉን ነገር አምቀን ተይ ውሎ ሲያድር አንድ ቀን ተይ ብንጣላ የለም የሚያስታርቀን ተይ እንዳንቀር ተራርቀን አማላጅ ለጊዜው ቢያስታርቅም እስከመጨረሻው አብሮ አይዘልቅም ተይ ሚስጥራችንን አሳልፈን ትዝብትና ጸጸት እንዳይተርፈን ወይ አልተለያየን ቁርጡን አውቀን ወይ አልተገናኘን ታርቀን በአንድ ቤት እያለን ከአንገት በላይ ምነው እንደደባል ባንተያይ ከኔም ካንቺም ቢሆን ጥፋቱ እያደር ይጠራል እውነቱ ጥላቻን በፍቅር ሰርዘን ብንኖር ይሻላል ታግሰን ተይ ተይ ተይ ረጋ ብለሽ አስቢ ተይ ይቅር ይቅር ይቅር ሰላም ይኑረን ተይ ተይ ተይ ተይ ረጋ ብለሽ አስቢ ተይ ይቅር ይቅር ይቅር ሰላም ይኑረን ተይ