Tezeta
Mahmoud Ahmed
5:46እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ (×2) ለፍቅር መለኪያ ቢኖረው ደረጃ አንቺን የምትበልጥ መገኘቷን እንጃ እርቀሽ እርቄሽ ከምትናፍቂኝ በቅርብ እንዳገኝሽ እባክሽ ታረቂኝ እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ(×2) አምናለሁ ማኩረፍሽ የምር እንዳይደለ ይቅር ተባብለን ብንኖር ምናለ ምናልባት ይሆናል ሳላውቅ አስቀይሜሽ የጥንቱን አስታውሽው ጨካኝ አይሁን ልብሽ እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ(×2) ቀንም እንዳልሰራ ለሊቱን በሀሳብ ባንቺ ፍቅር ብዛት እኔ ለምን ልራብ ስለዚህ አስቢ እስኪ በጥሞና ይታደስ ፍቅራችን ይጠቅመናልና እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ(×2) ካንቺ መለየቱ ሆነብኝ ዱብዳ እዘኝልኝና ድረሽ ሳልጎዳ ጠላት እንዲከፋው ደስ እንዲለው ወዳጅ አንቺ እኔን ታረቂኝ ይቅርብን አማላጅ እባክሽ እባክሽ ታረቂኝ ተይ አታስጨንቂኝ(×2)