Yager Betua Aynama

Yager Betua Aynama

Mahmoud Ahmed

Альбом: Birtukane
Длительность: 7:27
Год: 1980
Скачать MP3

Текст песни

ያገር ቤቷ አይናማ አንቺ ለግላጋ
አንቺ የገጠር መለሎ የገጠር ሎጋ
ልቤን ወዴት ሰወርሽው ሳይመሽ ሳይነጋ (አሃ)
ሳይመሽ ሳይነጋ

ያገር ቤቷ አይናማ አንቺ ለግላጋ
አንቺ የገጠር መለሎ የገጠር ሎጋ
ልቤን ወዴት ሰወርሽው ሳይመሽ ሳይነጋ (አሃ)
ሳይመሽ ሳይነጋ

በረፋዳው ምነው በረፋዳው በቀስተ ደመና
በወንዙ ዳር ምነው በወንዙ ዳር በምንጩ ጎዳና
ልቤን ነክሰሽ ምነው ሄደሽ ቀረሽ አንቺ መልከ ቀና
ላይኔ ባይሽ እኔስ ላይኔ ባይሽ ገና በጅምሩ
ወዲያው ፀንቶ ፍቅርሽ ወዲያው ፀንቶ ይዞኝ ከቀትሩ
ሸርተት አለ ድንገት ሸርተት አለ ከጄ ላይ በትሩ
ሸርተት አለ ድንገት ሸርተት አለ ከጄ ላይ በትሩ

አካል ልጅ ውበትሽ ኧረ እንዴት ይገርማል
ሰው መውደድ ያለ ሰው እንዴት ብሎስ ያልፋል
ልቤስ ባንቺ ነገር እጅጉን ይከፋል
ፍቅርሽ እንዴት ያልፋል

አካል ልጅ ናፍቆትሽ ኧረ እንዴት ይገፋል
ሰው መውደድ ያለ ሰው እንዴት ብሎስ ያልፋል
ልቤ ባንቺ ነገር እጅጉን ይከፋል
ፍቅርሽ እንዴት ያልፋል

መላው ጠፋኝ እንዴት መላ ልምታ
መላ አጣሁኝ እንዴት መላ ልምታ
ልቤን እየረታ
ዛሬስ አሸነፈኝ የቆንጆ ትዝታ

መላው ጠፋኝ እንዴት መላ ልምታ
መላ አጣሁኝ እንዴት መላ ልምታ
ልቤን እየረታ
ዛሬስ አሸነፈኝ የቆንጆ ትዝታ

ያገር ቤቷ አይናማ አንቺ ለግላጋ
አንቺ የገጠር መለሎ የገጠር ሎጋ
ልቤን ወዴት ሰወርሽው ሳይመሽ ሳይነጋ (አሃ)
ሳይመሽ ሳይነጋ

ያገር ቤቷ አይናማ አንቺ ለግላጋ
አንቺ የገጠር መለሎ የገጠር ሎጋ
ልቤን ወዴት ሰወርሽው ሳይመሽ ሳይነጋ (አሃ)
ሳይመሽ ሳይነጋ

ወደ ማታ እኔስ ወደ ማታ ዋርካው ስር ቁጭ ብዬ
በዋሽንቱ ሳዜም በዋሽንቱ ልቤን ካንቺ ጥዬ
ሳንጎራጉር ባንቺው ሳቀነቅን በመጣሽ አንቺዬ
በጨረቃው ምነው በጨረቃው የመሸነው ሳይነጋ
ወዴት ልሂድ እስቲ ከምን ልሂድ እኔ አንቺን ፍለጋ
ከየት ልይሽ የት ሰላም ልበልሽ አንቺ የገጠር ሎጋ
ከየት ልይሽ የት ሰላም ልበልሽ አንቺ የገጠር ሎጋ

አካል ልጅ ውበትሽ ኧረ እንዴት ይረሳል
አይንሽ ካይኔ መሀል ሌት ይመላለሳል
ልቤም አንቺን ብሎ ምንጭ ይገሰግሳል
ቢያጣሽ ይመለሳል

አካል ልጅ ውበትሽ ኧረ እንዴት ይረሳል
አይንሽ ካይኔ መሀል ሌት ይመላለሳል
ልቤም አንቺን ብሎ ምንጭ ይገሰግሳል
ቢያጣሽ ይመለሳል

መላው ጠፋኝ እንዴት መላ ልምታ
መላ አጣሁኝ እንዴት መላ ልምታ
ልቤን እየረታ
ዛሬስ አሸነፈኝ የቆንጆ ትዝታ

መላው ጠፋኝ እንዴት መላ ልምታ
መላ አጣሁኝ እንዴት መላ ልምታ
ልቤን እየረታ
ዛሬስ አሸነፈኝ የቆንጆ ትዝታ

ያገር ቤቷ አይናማ አንቺ ለግላጋ
አንቺ የገጠር መለሎ የገጠር ሎጋ
ልቤን ወዴት ሰወርሽው ሳይመሽ ሳይነጋ (አሃ)
ሳይመሽ ሳይነጋ
ልቤን ወዴት ሰወርሽው ሳይመሽ ሳይነጋ (አሃ)
ሳይመሽ ሳይነጋ

ያገር ቤቷ አይናማ አንቺ ለግላጋ
አንቺ የገጠር መለሎ የገጠር ሎጋ
ልቤን ወዴት ሰወርሽው ሳይመሽ ሳይነጋ (አሃ)
ሳይመሽ ሳይነጋ
ልቤን ወዴት ሰወርሽው ሳይመሽ ሳይነጋ (አሃ)
ሳይመሽ ሳይነጋ