Notice: file_put_contents(): Write of 631 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Shewandagne Hailu - Ayrega | Скачать MP3 бесплатно
Ayrega

Ayrega

Shewandagne Hailu

Альбом: Sik Alegn
Длительность: 4:46
Год: 2003
Скачать MP3

Текст песни

አይረጋ አይሰክን ይህ ልቤ
ይበታተን ጀመር ሀሳቤ

አይረጋ አይሰክን ይህ ልቤ
ይበታተን ጀመር ሀሳቤ
ለማን አዋያለው ችግሬን?
የማፍቀር የመውደድ ሚስጥሬን
አይረጋ አይሰክን ይህ ልቤ
ይበታተን ጀመር ሀሳቤ
ለማን አዋያለው ችግሬን?
የማፍቀር የመውደድ ሚስጥሬን

ልምድ አርጌው ለሰው ይምሰል መሳቄን
ማን አየብኝ ባንቺ ፍቅር መውደቄን?
በታደልሽው ገዳይ ውበት ማርከሽኝ
ቶሎ የማይሽር የልብ ህመም ሰጠሽኝ
ልምድ አርጌው ለሰው ይምሰል መሳቄን
ማን አየብኝ ባንቺ ፍቅር መውደቄን?
በታደልሽው ገዳይ ውበት ማርከሽኝ
ቶሎ የማይሽር የልብ ህመም ሰጠሽኝ

ጥሎበት ይህ ልቤ አንቺን ወዶ
ኑሮን ከሌላ ሰው መቼ ለምዶ
ሲያስብሽ ይኖራል መሸም ነጋ
አልሰክን እያለኝ ልቤ አይረጋ
ጥሎበት ይህ ልቤ አንቺን ወዶ
ኑሮን ከሌላ ሰው መቼ ለምዶ
ሲያስብሽ ይኖራል መሸም ነጋ
አልሰክን እያለኝ ልቤ አይረጋ

አይረጋ አይሰክን ይህ ልቤ
ይበታተን ጀመር ሀሳቤ

አይረጋ አይሰክን ይህ ልቤ
ይበታተን ጀመር ሀሳቤ
ለማን አዋያለው ችግሬን?
የማፍቀር የመውደድ ሚስጥሬን
አይረጋ አይሰክን ይህ ልቤ
ይበታተን ጀመር ሀሳቤ
ለማን አዋያለው ችግሬን?
የማፍቀር የመውደድ ሚስጥሬን

የማዋየው ሰውም የለኝም ጓደኛ
ሆኛለሁኝ ባይተዋር ሰው ብቸኛ
ከምወደው አስበልጬሽ ከራሴ
አንቺን ሳስብ አልረጋ አለኝ መንፈሴ
የማዋየው ሰውም የለኝም ጓደኛ
ሆኛለሁኝ ባይተዋር ሰው ብቸኛ
ከምወደው አስበልጬሽ ከራሴ
አንቺን ሳስብ አልረጋ አለኝ መንፈሴ

ጥሎበት ይህ ልቤ አንቺን ወዶ
ኑሮን ከሌላ ሰው መቼ ለምዶ
ሲያስብሽ ይኖራል መሸም ነጋ
አልሰክን እያለኝ ልቤ አይረጋ
ጥሎበት ይህ ልቤ አንቺን ወዶ
ኑሮን ከሌላ ሰው መቼ ለምዶ
ሲያስብሽ ይኖራል መሸም ነጋ
አልሰክን እያለኝ ልቤ አይረጋ
ጥሎበት ይህ ልቤ አንቺን ወዶ
ኑሮን ከሌላ ሰው መቼ ለምዶ
ሲያስብሽ ይኖራል መሸም ነጋ
አልሰክን እያለኝ ልቤ አይረጋ
ጥሎበት ይህ ልቤ አንቺን ወዶ
ኑሮን ከሌላ ሰው መቼ ለምዶ