አድራሻዬ
Tamirat Haile
6:12ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን በ ማላኪቲ አጃቢ በ እግዛኢያቢሀር ማላካቲ ኢየሱስ ፡ ይመጣል ፡ ከላይ ፡ ከሰማያት የአባቴ ፡ ብሩካን ፡ ኑ ፡ እረፉ ፡ ይለናል እንደ ፡ ድካማችን ፡ ዋጋ ፡ ይከፍለናል ተስፋ ፡ እንደሌላችሁ ፡ ፈጽሞ ፡ አትዘኑ እርስ ፡ በእርሳችሁም ፡ በዚህ ፡ ቃል ፡ ተጽናኑ ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን በጌታ ፡ የሞቱ ፡ ቀድመው ፡ ይነሳሉ ሰማያዊ ፡ አካል ፡ ፈጥነው ፡ ይለብሳሉ እኛ ፡ ሕያዋን ፡ እንለወጣለን አብረን ፡ በደመና ፡ እንነጠቃለን ተስፋ ፡ እንደሌላችሁ ፡ ፈጽሞ ፡ አትዘኑ እርስ ፡ በእርሳችሁም ፡ በዚህ ፡ ቃል ፡ ተጽናኑ ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን ዓለም ፡ በክፋቷ ፡ እየባሰች ፡ ሄደች ሕያዋንን ፡ አልፋ ፡ በድን ፡ አሳደደች አዲስ ፡ ነገር ፡ የለም ፡ ነው ፡ እንደተጻፈው በክርስቶስ ፡ ትዕግስት ፡ ሁሉን ፡ እንለፈው የሚረዳን ፡ ጸጋ ፡ ጌታ ፡ ይሰጠናል ኋላም ፡ በመምጣቱ ፡ በክብር ፡ ይገልጠናል ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን ጌታ ፡ የሚዘገይ ፡ መስሎ ፡ ቢታያቸው በዚህ ፡ ዓለም ፡ አምላክ ፡ ታውሮ ፡ ዐይናቸው እንደ ፡ ተስፋ ፡ ቃሉ ፡ አይዘገይም ፡ በእውነት እንደ ፡ ሌባ ፡ ሆኖ ፡ ይመጣል ፡ በድንገት የወጉት ፡ ያዩታል ፡ በዘውድ ፡ አሸብርቆ በግርማው ፡ ሲገለጥ ፡ ከከዋክብት ፡ ደምቆ ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን ነቀፋና ፡ ስድብ ፡ ስደትና ፡ ዛቻ የጠላት ፡ ተግዳሮት ፡ የዘመድ ፡ ጥላቻ እጦትና ፡ ህመም ፡ ሃዘንና ፡ እሮሮ ያለው ፡ የሚመጣው ፡ ሁሉም ፡ ተደምሮ ይገለጥ ፡ ዘንድ ፡ ካለው ፡ ሰማያዊ ፡ ክብር ያሁን ፡ ዘመን ፡ ስቃይ ፡ አይወዳደር ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ መከራ ፡ እናልፋለን በቀኑ ፡ መጨረሻ ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ እንደፋለን