እምነት ሲለካ በስፍር
Tamirat Haile
8:21ምድር ለሰው ልጆች ተሰጥታለች አልፋ ፣ ተሰጥታለች አልፋ ሁሉም በየሙያው ይላል ቀና ደፋ ፣ ይላል ቀና ደፋ ከዚህ ወዲያ ይባል ከዛ በመለስ ፣ ከዚያ በመለስ ቅዱሱ ይቀደስ እርኩሱም ይርከስ ፣ እርኩሱም ይርከስ አይቶ ስምቶ የለየ ፣ ነፃነት አለዉ እንስበከው እንጂ ፣ ጡንቻ እናሳየው ያሻውን ይከተል ፣ ሰው እንደገባው ሰይፋችን ይመለስ ፣ ወደ ሠገባው ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ (ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ) ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን (ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን) ምድር ተባርካለች በሃይማኖት ብዛት ፣ በሃይማኖት ብዛት ህማሟ ባሠ እንጂ ፣ አንዱም አልፈወሳት ፣ አንዱም አልፈወሳት ምድር ተባርካለች በሃይማኖት ሃብት ፣ በሃይማኖት ሃብት እንትን እና እንትን እንትን በሚሉት ፣ እንትን በሚሉት አሁንም ይፈልቃል ፣ በየቀበሌው እናትና አባት አያት የሌለው አንዱ ካላዳነ ፣ አያድንም ሺሁ ወገኔ ተመለስ ፣ ይቅርብህ እልሁ ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ (ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ) ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን (ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን) በስራ ይገለጥ የያዝነው እምነት ፣ የያዝነው እምነት ሙታንም ይነሱ ይወጡ አጋንንት ፣ ይወጡ አጋንንት ዳንኩኝ ተፈወስኩኝ ብለው ይመስክሩ ፣ ብለው ይመስክሩ የሃይማኖት ፋይዳ ይህ ነው ቁም- ነገሩ ፣ ይህ ነው ቁም-ነገሩ የሚያድን እምነት ፣ የሚያደርስ ሰማይ ከሌለው ሰው አርፎ ፣ ሠርቶ አይበላም ወይ በሰላም አንደር ፣ አይረበሽ ሠፈር ድንበር አትለፉ ፣ ተዉ አንደፋፈር ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ (ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ) ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን (ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን) ደርሶ ስም ለማጥፋት ወሬ አሉባልታ ፣ ወሬ አሉባልታ ጭራሽ ይባስ ብሎ ባስክሬን ጨዋታ ፣ ባስክሬን ጨዋታ ትዳርን አፋቶ ልጅ ከናት ነጥሎ ፣ ልጅ ከእናት ነጥሎ ከቀዬ ከሠፈር ከማህበር አግልሎ ፣ ከማህበር አግልሎ ከገነት ሊገባ እንዲያው መታሰቡ ፣ ቁርጥህን እወቀው አትደርስ ካጠገቡ አሳደው እሠራው ግደልልኝ ያለ ፣ ዲያቢሎስ ነው እንጂ እግዚያብሔር አይደለ ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ (ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ) ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን (ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን) የኔ ይበልጣል ቢሉ ምንም ክፋት የለው ፣ ምንም ክፋት የለው እኛ ማንስማማው ዛቻ ሲጀመር ነው ፣ ዛቻ ሲጀመር ነው እግዚያብሔር ትልቅ ነው ለሁሉም ሚበቃ ፣ ለሁሉም ሚበቃ ምስክር ነው እንጂ አያሻው ጠባቃ ፣ አያሻው ጠባቃ እናንተ የአምላክ ልጆች ፣ ከቶ አትታወኩ ሁሉም በየቋንቋው ፣ ይጩህ ወዳምላኩ የሁሉም ማንነት ፣ በተግባር ይታያል የኤልያስ አምላክ ፣ በእሳት ይለያል ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ (ስምቶ የሚመልስ ፣ በእኛ ላይ ይንገስ) ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን (ወርዶ የሚያድን ፣ እርሱ አምላክ ይሁን)