Notice: file_put_contents(): Write of 644 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Temesgen Markos - Nurelet Legeta | Скачать MP3 бесплатно
Nurelet Legeta

Nurelet Legeta

Temesgen Markos

Альбом: Sew Biteyek
Длительность: 5:33
Год: 2019
Скачать MP3

Текст песни

እንደልቡ ሃሳብህን ልክ እንደ ፈቃዱ
ለእርሱ የተለዩለት ለአንዱ ለሰገዱ
መስለውት በመኖር ጌታን ላስከበሩ
ዋጋ አለ ከእርሱ ዘንድ ሲመጣ በክብሩ

ስለዚህ ወገኔ አስብ አስተውል
በዚህች ዓለም ነገር እንዳትታለል
አንድ ቀን ወደላይ በክብር ከእርሱ ጋር
ስትሄድ በደመና ወደ አምላክ እግዚአብሔር

የዘለዓለም ደስታ የሁልጊዜ እረፍት
ሃዘን በሌለበት ደስ የሚያሰኝ ገነት
ትኖራለህ በዚያች ቅድስቲት ከተማ
ስለዚህ ወገኔ ከእርሱ ጋር ተስማማ

ኑርለት ኑርለት ለጌታ
ኑርለት ኑር እንደሃሳቡ
ኑርለት ኑር እንደፈቃዱ
ያን ጊዜ ታያለህ
እርሱ አንተን መውደዱ

እንደፈቃድህ መኖርን መኖርን አስተምረኝ
ለሃሳብህ መኖርን መኖርን አለማምደኝ
ለፈቃድህ መኖርን መኖረን አስተምረኝ
ለሃሳብህ መኖርን መኖርን አለማምደኝ

ልኑር ልኑር
እንደ ፈቃድህ ልኑር
እንደ ሃሳብህ ልኑር
ፀጋህ ይርዳኝ ጉልበት ስጠኝ
እኔ አልችልም ባክህ አግዘኝ

አውቀህ አገልግለህ አምላክህን በክብር
ሚገባውን መጽዋት አቅርብ ከእግሩ ስር
ከቶ እንዳትሰማ የጠላትን ወሬ
ክብርህ ኢየሱስ ነው አስተውል ወገኔ

ለአፍታ እንዳትዘነጋ የመቆምህን ሚስጥር
ዛሬን የማየትህ በእርሱ ነው በእግዚአብሔር
ክብርና ዝና ሃብት ስላለህ ሳይሆን
ስለመረጠህ ሰው ስለለየህ አንተን

ኑርለት ኑርለት ለጌታ
ኑርለት ኑር እንደሃሳቡ
ኑርለት ኑር እንደፈቃዱ
ያን ጊዜ ታያለህ
እርሱ አንተን መውደዱ

እንደፈቃድህ መኖርን መኖርን አስተምረኝ
ለሃሳብህ መኖርን መኖርን አለማምደኝ
ለፈቃድህ መኖርን መኖረን አስተምረኝ
ለሃሳብህ መኖርን መኖርን አለማምደኝ

ልኑር ልኑር
እንደ ፈቃድህ ልኑር
እንደ ሃሳብህ ልኑር
ፀጋህ ይርዳኝ ጉልበት ስጠኝ
እኔ አልችልም