Notice: file_put_contents(): Write of 637 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Tesfaye Chala - Mister | Скачать MP3 бесплатно
Mister

Mister

Tesfaye Chala

Длительность: 5:23
Год: 2018
Скачать MP3

Текст песни

ሚስጥር ፡ አለ ፡ ልቤ (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
ለሰው ፡ ያልነገርኩት (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
አብረውኝ ፡ ለበሉ (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
ያላጨዋወትኩት (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
ዙሪያዬ ፡ ጸጥ ፡ ሲል (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
በሮቼን ፡ ዘግቼ (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
ልንገረው ፡ ለአምላኬ (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
የሆዴን ፡ ገልጬ (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
እዩት ፡ ይሄ ፡ ልቤን ፡ እየተሸከመ
ብቻውን ፡ አምቆት ፡ ብቻውን ፡ ታምኖ
ዛሬ ፡ ዙፋኑ ፡ ስር ፡ ሸክሜን ፡ ልጣለው
እስከመቼ ፡ ልዘን ፡ አምላክ ፡ እንደሌለው
ወዳጅ ፡ እንደሌለው
አዝ ፦ ደረሰ ፡ ጊዜው ፡ ሰዓቱ ፡ የአምላኬን ፡ ፊት ፡ የማይበት
መንፈሴን ፡ ላዋርድ ፡ እራሴን ፡ ዝቅ ፡ ይበል ፡ ይምበርከክ ፡ ጉልበት
በስውር ፡ የለመንኩትን ፡ በግልጽ ፡ እርሱ ፡ እንደሚከፍለኝ
ሸክሜን ፡ ልጣል ፡ እግሩ ፡ ስር ፡ መጽሃፍ ፡ እንደነገረኝ (፪x)
ለካስ ፡ አለጉዳይ (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
ለሰው ፡ የማይነግሩት (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
ወይ ፡ በሆድ ፡ ደብቀው (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
የማያባብሉት (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
አምቄ ፡ ደብቄ (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
እስከመቼ ፡ ልጐዳ (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
ልንገረው ፡ በእምባዬ (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
ሰምቶ ፡ ለሚረዳ (ሚስጥር ፡ ሚስጥር)
መጐዳቴን ፡ አይቶ ፡ ዘምበል ፡ ይልልናል
ሰምቶ ፡ እንዳልሰማ ፡ መቼ ፡ ጥሎ ፡ ያልፋል
ለእርሱ ፡ እነግረዋለሁ ፡ አልፈልግም ፡ ለሰው
የልቤን ፡ ዘርግፌ ፡ እገላገላለሁ (፪x)
አዝ ፦ ደረሰ ፡ ጊዜው ፡ ሰዓቱ ፡ የአምላኬን ፡ ፊት ፡ የማይበት
መንፈሴን ፡ ላዋርድ ፡ እራሴን ፡ ዝቅ ፡ ይበል ፡ ይምበርከክ ፡ ጉልበት
በስውር ፡ የለመንኩትን ፡ በግልጽ ፡ እርሱ ፡ እንደሚከፍለኝ
ሸክሜን ፡ ልጣል ፡ እግሩ ፡ ስር ፡ መጽሃፍ ፡ እንደነገረኝ (፪x)
አዝ ፦ ደረሰ ፡ ጊዜው ፡ ሰዓቱ ፡ የአምላኬን ፡ ፊት ፡ የማይበት
መንፈሴን ፡ ላዋርድ ፡ እራሴን ፡ ዝቅ ፡ ይበል ፡ ይምበርከክ ፡ ጉልበት
በስውር ፡ የለመንኩትን ፡ በግልጽ ፡ እርሱ ፡ እንደሚከፍለኝ
ሸክሜን ፡ ልጣል ፡ እግሩ ፡ ስር ፡ መጽሃፍ ፡ እንደነገረኝ (፬x)