Ayeqerm Andsew
Tewodros Tadesse
5:09በከተማዉ በመንደሩ በአካባቢው በሀገሩ ሆዴ ነይልኝ ሆዴ ነይልኝ ያላንቺም የለኝ ሆዴ ነይልኝ ሆዴ ነይልኝ ያላንቺም የለኝ እንክርዳድ በብርሃን የተለቀመልሽ ገለባዉ በሌባ የተበጠረልሽ ቀን ከሌት አስደዉሮ ለዉበት የወጠነሽ ሲያወጣ ሲያወርድ ዉሎ እንዴት ነው የከሸነሽ የጥበብ ወሰኑ ነሽ እንከን ያልጣለብሽ ለአመል ለመዉቀሻ ስበብ የታጣብሽ ለጥፋት መጥቀሻ አምላክ በቀን ጀምሮ ቅን አርጎም የጨረስሽ በፅንነት ገንብቶ በዉበት የጨረሰሽ በምን ቀን ነዉ ያነፀሽ ተወኝ ሆዴ ማዘኑን የሌቱንም የቀኑን ተወኝ አይኔ ብክነቱን ከጎዳናዉ ማየቱን ልቤም ፍቅርሽ ቢሰማዉ ንፁ አመልሽ ቢስማማዉ አንቺን አለ ካገር ከከተማው በከተማው በመንደሩ በአካባቢው በሀገሩ ሆዴ ነይልኝ ሆዴ ነይልኝ ያላንችም የለኝ በከተማው በመንደሩ በአካባቢው በሀገሩ ሆዴ ነይልኝ ሆዴ ነይልኝ ያላንችም የለኝ ከንተርታ መንፈሴ አይቶ ተመልክቶ ጭንቀቴን ሊመልስ በጥበብ መክቶ ሊያፅናናኝ ነዉ መሰለኝ ሀዘኔም ገርበብ አለ ለፍቅር ብድር ሰጠኝ ዉለታን በኔ ዋለ አንቺን እያስከተለ ችግር በቃ ብሎ ፊቱን ከመለሰ የኔም ብቸኘነት ግምቡ ከፈረሰ አንቺን ከፍሎ ከካሰኝ አምላክ ጎኔን ከረዳዉ ተንጎራደጂ ከእልፍኙ በይ ከጓዳዉ ላንቺዉ ነዉ ቤቴ የፀዳዉ ተወኝ ሆዴ ማዘኑን የሌቱንም የቀኑን ተወኝ አይኔ ብክነቱን ከጎዳናዉ ማየቱን ልቤም ፍቅርሽ ቢሰማዉ ንፁ አመልሽ ቢስማማዉ አንቺን አለ ካገር ከከተማው ተወኝ ሆዴ ማዘኑን የሌቱንም የቀኑን ተወኝ አይኔ ብክነቱን ከጎዳናዉ ማየቱን ልቤም ፍቅርሽ ቢሰማዉ ንፁ አመልሽ ቢስማማዉ አንቺን አለ ካገር ከከተማው ተወኝ ሆዴ ማዘኑን የሌቱንም የቀኑን ተወኝ አይኔ ብክነቱን ከጎዳናዉ ማየቱን ልቤም ፍቅርሽ ቢሰማዉ ንፁ አመልሽ ቢስማማዉ አንቺን አለኝ ካገር ከከተማው