Bemewadedachin
Tewodros Tadesse
4:58እምዬ ኢትዮጵያ ይመርልሽ ሰብሉ አውድማው ጎተራው ይሁንልሽ ሙሉ በቸር ውሎ ይደር ጋራ ሸንተረርሽ ወንዛወንዝሽ ሁሉ ይመስክር አካሌ ጉያሽ ያደረጀው የእናትነት ጣምሽ ውለታሽ ያበጀው በማጀትሽ ወተት በጤፍሽ እንጀራ በማር በወለላ በጓሮ ሸንኮራ ብድር አለብኝ ልክፈልና ልኩራ ክብርሽ ከፍ ይበል ከሰላምሽ ጋራ የወለደኝ ምጥሽ በቸር ዉሎ ይደር ያሳደገኝ ቀዬሽ በቸር ዉሎይደር ወንዝና ጅረትሽ በቸር ዉሎ ይደር ጫካውና ደንሽ በቸር ዉሎ ይደር አውድማና ማሳሽ በቸር ዉሎ ይደር በቸር ውሎ ይደር በቸር ዉሎ ይደር በቸር ዉሎ ይደር ዙሪያው በቸር ዉሎይደር በቸር ዉሎ ይደር ያሳደገኝ መንደር በቸር ዉሎይደር እምዬ ኢትዮጵያ ይመርልሽ ሰብሉ አውድማው ጎተራው ይሁንልሽ ሙሉ በቸር ውሎ ይደር ጋራ ሸንተረርሽ ወንዛወንዝሽ ሁሉ ያበቀለኝ ቀዬ የተወለድኩበት ያበብኩበት ምድርሽ ባካል ያሸትኩበት ሜዳውና መስኩ የፈነደኩበት ያደኩበት ወንዝሽ የተራጨሁበት ክፉም አልስማ ክፉም አልይበት ሰላም ደምኖ ሰላም ይዝነብበት የእናት ያባቴ አገር በቸር ዉሎ ይደር የወገኔ ተገን በቸር ዉሎ ይደር የትውልዴ መድን በቸር ዉሎ ይደር አፈሩም ሰፈሩም በቸር ይደር ዓየሩም ባሕሩም በቸር ይደር በቸር ውሎ ይደር በቸር ዉሎ ይደር በቸር ዉሎ ይደር ዙሪያው በቸር ዉሎ ይደር በቸር ዉሎ ይደር ያሳደገኝ መንደር በቸር ይደር ዙሪያው በቸር ዉሎ ይደር ያደኩበት አገር በቸር ይደር ዙሪያው በቸር ይደር ያሳደገኝ መንደር