Lebo
Theodros Kassahun
5:45ቀዘብዬ የኔ ቀዘባ የኔ ቀዘባ ስልሽ ጥላዬ የማለዳ ሲሳይ የጠዋት እጣዬ ነይ ወላባዬ እህል ውሃ ሞልቶ አንቺው ነሽ እርሃቤ ሆዴስ ነገር በላ ጦም አደረ ልቤ ቀናተኛ ብሎ ሰው በኔ ፈረደ መጠርጠሩ ላይቀር እሸት የወደደ ጀምበር ተሰናብታ ሰማዩም ጠቆረ ደሞ እንደ ልማዴ ይጨንቀኝ ጀመረ ቀልቤም አይሰክንልኝ ካንቺው ነው ሐሳቤ ወተሽ እስክትገቢ መች የረጋል ልቤ በናፍቆ በናፍቆት ተረታሁኝ እኔ እንግዲ ማን ይሁን ለብቸኛው ጎኔ ለሳቅ ለጨዋታ ባይገደብ ጥርሴ መች ቀረ በሆዴ ነገር መጠንሰሴ ተኳኩሎ መውጣት መሄድሽ ካልቀረ አንድ ሕመም አያጣም ክፉ አመል ካደረ እኔ ከደጅ ውዬ ስመለስ ባጣሽም ምንምቅር ቢለኝ ቂም አሊዝብሽም ለጊዜው ነው እንጂ ሆዴን የሚብሰው ህርም የለኝም ላንቺ አልተካሽም በሰው በናፍቆት በናፍቆት ተረታሁኝ እኔ እንግዲ ማን ይሁን ለብቸኛው ጎኔ በናፍቆት በናፍቆት ተረታሁኝ እኔ እንግዲ ማን ይሁን ለብቸኛው ጎኔ እንዲያው ሰበብዬ... እንዲያው ቀዘብዬ...