Yaekob Kebersabeh
Yilma Hailu
ለእኔስ ልዩ ነሽ ድንግል ማርያም ለእኔስ ልዩ ነሽ እመብርሃን ፈልጌ ፈልጌ(፪) ለአንቺ ምሥጋና አላገኘሁም ልቤ ሲያበቅል የኃጢአት አረም ውስጤ ሲሸፍት አልተወችኝም ከቤተ መቅደስ እጇን ዘርግታ ትጠራኛለች የኔ መከታ አዝ የሆዴን ሀዘን የልቤን ሚሥጢር እነግርሻለሁ አንድም ሳይቀር የምትሸሽጊ የህዝብን ኃጢአት ለእኔስ ልዩ ነሽ ድንግል አዛኝት አዝ ጣዕሙ ልዩ ነው ከአንቺ ጋር መኖር ድንግልን ይዤ መቼም አላፍር ወደ ጽድቅ ሕይወት ትወስደኛለች ድንግል ማርያም ለእኔ እናቴ እኮ ነች አዝ በሐዘን ስሰበር ማንን ጠራለሁ ውሥጤ ሲደማ ለማን ነግራለሁ ከኃጢአት እድፍ ንጹህ መሆኛዬ አንቺ ነሽ ለኔ ለእኔስ መጽናኛዬ አዝ የኃጢአት ቁስል ያለአንቺ አይጠግም ልጅሽ ሣይፈቅድ በሕይወት አልኖርም ከልጅሽ ሌላ መድኅን የለኝም ከጸሎት በቀር ፍጹም አልድንም