Amlake Destaye
Yohannes Girma
6:14መቅበዝበዝ ሳበዛ በዓለም ስዋትት ክብር መስሎኝ ታይቶኝ ውርደት ሳካብት በበደሌ ብዛት ሞት የሚገባኝን ፀጋህን አብዝተህ በህይወት ኖርኩኝ ዛሬ ለአንተ ቆሜ በአፌ እዘምራለሁ ያዳንከውን አዳዳን ገድልህን አወራለሁ ግነን በዓለማት ስምህ ከፍ ይበል በእርግጥ ከዚህ በቀር የለም የምከፍልህ አንተን ያገኘሁ ዕለት መንገዴ ተቃና በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና ምክርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያጸድቃል አንተን ያገኘሁ ዕለት መንገዴ ተቃና በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና ምክርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያጸድቃል ስንከራተት ሳለሁ በምድረ በዳ ላይ የሚረዳኝ የለ ግራ ቀኜን አላይ ባልጠበኩት ቦት ከሰማይ ድምጽ መጣ እጁ እጄን ያዘ ተራራ አወጣኝ አንተ የኔ እኮ ነህ ልጄ እወድሃለሁ በእውነት ቃል አስቤ ለክብር ወልጄሃለው ለዘላለም ፍቅሬ ከአንተ አትለይም አለኝ ለዘላለም እኔ አልጥልህም አንተን ያገኘሁ ዕለት መንገዴ ተቃና በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና ምክርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያጸድቃል እርጥበት የማያውቅ በድርቅ የደቀቀ ህይወቴ ነበረ ከአጥንት የደረቀ ከፍጥረቴ ሳለሁ የበረሀ ወይራ መጠጊያን አገኘሁ በመልካሙ ስፍራ ምሁሩን ሊያስቀና ምስኪኑን መረጠ ከውርደት አንስቶ ለክብር አስቀመጠ በእሱ ተተክዬ በመልካሙ ግንድ ዘር ልምላሜን አገኘሁ ለዘላለም ይክበር አንተን ያገኘሁ ዕለት መንገዴ ተቃና በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና ምክርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያጸድቃል ጠመዝማዛ ጉዞ ቁልቁለት ሳዘግም ሞቴን ለማፋጠን ሀጢያትን ስቃርም በጠላት ድለላ በእሱ ጦር ታጅቤ ከፍቅር አባቴ ከአንተ ሲሸሽ ልቤ እንደ ህፃን አርገህ በእርጋታ መከርከኝ ሳላውቅ እንዳልጠፋ ፍቅርህ ሰበሰበኝ አንተ ካስጠጋኸኝ የሚከሰኝ ማነው ነጻ ያወጣኸኝ ከልብህ ወደኸኝ ነው አንተን ያገኘሁ ዕለት መንገዴ ተቃና በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና ምክርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያጸድቃል አንተን ያገኘሁ ዕለት መንገዴ ተቃና በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና ምክርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያጸድቃል