Kehatyategnaw Denkuan
Zemari Deacon Abel Mekbib
5:32ምልክቴ ነሽ ድንግል ለህይወቴ ባንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ ጸጋሽ ጎብኝቶኝ ቃልኪዳንሽ ምልክቴ ነሽ ድንግል ለህይወቴ ባንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ ጸጋሽ ጎብኝቶኝ ቃልኪዳንሽ ተስፋ ያርኩት አልተበተነም እንባዬ ማሬት ከቶ አልወደቀም ለበጎ ሆነ ማልቀስ ማንባቴ ሰላም ሰፈነ በእልፍኝ በቤቴ ቅኔ ነጠኩኝ ያባ ጊዮርጊስን ቆምኩኝ ቅዳሴ የሕርያቆስን የያሬድ ዜማ ሞላ በልቤ የለም ወጀቡ ቀርባኝ መርከቤ ምልክቴ ነሽ ድንግል ለህይወቴ ባንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ ጸጋሽ ጎብኝቶኝ ቃልኪዳንሽ ወገቤን ታጠኩ ጭንቀቴን ጥዬ ዛሬስ በድስታ ይፍሰስ እንባዬ የኃዘን ልብሴን ድንግል ቀይራ የደበዘዘው ሕይወቴ በራ አራራይ ዜማ ዛሬ ተማርኩኝ ፍቅሯ አሽነፈኝ እጄን ሰጠሁኝ ቅኔ በልቤ ተመላለሰ የድንግል ክብር ዉስጤ ነገሰ ምልክቴ ነሽ ድንግል ለህይወቴ ባንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ ጸጋሽ ጎብኝቶኝ ቃልኪዳንሽ የዘረጋሁት እጄ ተሞላ ማርያም ሆናልኝ ጥላ ከለላ የዉስጤ ፀሎት ዛሬ ሌላ ነው የድንግል ክብር ምልጃው ቀየረው ዛሬ ጎጆዬ አንፀባረቀች ያማረ ሰንፔር እንቁ መሰለች ቀንዴ ከፍ ከፍ አለልኝና ሰዋሁ ለድንግል ይህን ምስጋና ምልክቴ ነሽ ድንግል ለህይወቴ ባንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ ጸጋሽ ጎብኝቶኝ ቃልኪዳንሽ ምልክቴ ነሽ ድንግል ለህይወቴ ባንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ ጸጋሽ ጎብኝቶኝ ቃልኪዳንሽ