Mindinew Zimtash

Mindinew Zimtash

Zerubabel Mola

Альбом: Enfalot
Длительность: 4:34
Год: 2019
Скачать MP3

Текст песни

ምንድነው ዝምታው
ምንድነው ዝምታሽ
ምንድነው ዝምታው
ምንድነው ዝምታሽ
በክፉ በደጉ ሳንለያይ
ሊያሳስቱሽ ነው ወይ
ምንድነው ዝምታው
ምንድነው ዝምታሽ
ምንድነው ዝምታው
ምንድነው ዝምታሽ
በክፉ በደጉ ሳንለያይ
ሊያሳስቱሽ ነው ወይ

ላንቺም ለኔም ከቶ የማይበጁ
ጥጥ ሸምነው ጋቢ እየቋጩ
ያሞጋገሱሽ ምን እንኳን ቢመስልም
ነጠላቸው ብርድ አያስጥልም
እንኳንስ ለኛ ለሃገሩ ሊያውቁ
ለራሳቸው ከቶ የት አወቁ
ባንቺ ዝምታ ጎን እየታከኩ
ጎጆዋችንን ስሩን ነካኩ

እናትዬ ጥንስሱን እይዉ
እታለሜ ድግሱን ለይው
እናትዬ ጥንስሱን እይዉ
እታለሜ ድግሱን ለይው

ምንድነው ዝምታው
ምንድነው ዝምታሽ
ምንድነው ዝምታው
ምንድነው ዝምታሽ
በክፉ በደጉ ሳንለያይ
ሊያሳስቱሽ ነው ወይ

የሚያስቡልን እየመሰሉ
ገብተው ከቤት ጠብ ሲያማስሉ
ጥል እንደ እንጀራ እያጎረሱ
የስንቱን ቤት አፈራረሱ
እነሱ የመከሯት የሰማቻቸው
ነውር እርቃኗን ወጥታ ታየችው
እመቤትነቷ የነበረው ክብሯ
ተገፈፈ ለከርሞ አሳሯ

እናትዬ ጥንስሱን እይዉ
እታለሜ ድግሱን ለይው
እናትዬ ጥንስሱን እይዉ
እታለሜ ድግሱን ለይው

ምንድነው ዝምታው
ምንድነው ዝምታሽ
ምንድነው ዝምታው
ምንድነው ዝምታሽ
በክፉ በደጉ ሳንለያይ
ሊያሳስቱሽ ነው ወይ

እናትዬ ጥንስሱን እይዉ
እታለሜ ድግሱን ለይው
እናትዬ ጥንስሱን እይዉ
እታለሜ ድግሱን ለይው
እናትዬ ጥንስሱን እይዉ
እታለሜ ድግሱን ለይው
እናትዬ ጥንስሱን እይዉ
እታለሜ ድግሱን ለይው