Notice: file_put_contents(): Write of 637 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Agegnehu Yideg - Enamnalen | Скачать MP3 бесплатно
Enamnalen

Enamnalen

Agegnehu Yideg

Альбом: Bizu Yehonkilign
Длительность: 6:26
Год: 2021
Скачать MP3

Текст песни

እናምናለን እናምናለን
እኛም ተጐብኝተን እናያለን
እናምናለን እናምናለን
የእግዚአብሔርን ክብር እናያለን
እናምናለን እናምናለን
ኢትዮጵያም ተጐብኝታ እናያለን
እናምናለን እናምናለን

አዲስን ነገር እናያለን
የመጐብኛችን ቀን ደርሶ
የእግዚአብሔር ኃይል ከላይ ወርዶ
ልመናዋ ተሰምቶላት
ለቤተ ክርስቲያን
እናያለን ገና በጌታ
ጥማት ተለውጦ በእርካታ

እናያለን ብዙ በጌታ
ያስለቀሰን ሁሉ ሲመታ

እናምናለን እናምናለን
ስድባችን ተወግዶ እናያለን
እናምናለን እናምናለን
ፀሎት ተመልሶ እናያለን

ለሰዎች ጥያቄ ሆነን
እስከ መቼ እንኖራለን
በስውር የለመንነውን
በግልፅ እንቀበላለን

መቼ እንዳለቀሰች ትቀራለች
ሃናም ሳሙኤልን ትወልዳለች
መቼ እንዳለቀሰች ትቀራለች
ሣራም ይስሐቅን ትወልዳለች

እናምናለን እናምናለን
መካኒቱ ወልዳ እናያለን
እናምናለን እናምናለን
አዲስን ነገር እናያለን

የእግዚአብሔር ክብር ሲገለጥ
ማነው በፊቱ የሚቆመው
አጋንንት ኃጢአት በሽታ
ይወገዳሉ ፈፅመው

የታሰሩት ሁሉ ይፈታሉ
ለአምላካቸው ክብርን ይሰጣሉ
አመፀኞች ሁሉ ይማረካሉ
ለኢየሱሴ ክብር ይሰግዳሉ

እኔ እናምናለሁ እኔ እናምናለሁ
የጌታን ተዓምራት አያለሁ
እኔ እናምናለሁ እኔ እናምናለሁ
ገና በሕይወት እኖራለሁ

ጠላቴ ቢገለኝ ሁሌ ቢፈልገኝም
ዛሬም በሕይወት አለሁ ከቶ አላገኘኝም
በቀረው ዘመን ወዴት ያገኘኛል
ገና እንደምኖር ጌታ ተናግሮኛል
በቀረው ዘመን ወዴት ያገኘኛል
እንደማገለግል ጌታ ተናግሮኛል

አልሞትም በሕይወት እኖራለሁ
የጌታዬን ማዳን ገና ዘምራለሁ
አልሞትም በሕይወት እኖራለሁ
የኢየሱሴን ሥራ ገና እሰራለሁ

ገና ለእግዚአብሔር አስፈልገዋለሁ
በጨለማ ላሉ ብርሃን ሆናለው
መከሩ ብዙ ነው ብዙ ነፍስ ሰው ይድናል
በሕይወት እያለሁ ተስፋው ይፈፀማል

አልሞትም በሕይወት እኖራለሁ
የዲያቢሎስን ሥራ ገና አፈርሳለሁ

ባለፈው ዘመኔ ምንም ብበድለው
የዘለዓለም አምላክ ዛሬም ከእኔ ጋር እንው
በማልጠቅመው በኩን ሥራውን ይሰራል
ደስ አሰኘዋለሁ በእኔው በልጁ ይከብራል

አልሞትም በሕይወት እኖራለሁ
በእግዚአብሔር ፀጋ አገለግላለሁ
አልሞትም በሕይወት እኖራለሁ
በእግዚአብሔር ቤት እለመልማለሁ