Mistren Yemigelts
Azeb Hailu
4:38ከሰማይ የመጣው የውዴ ውብ ቃል ልጄ ወዳጄ ሆይ አንቺ የኔ ሲል በኮረብታዎች ላይ መጣልኝ ሲዘል ሐዘኔን ሊያስረሳ ነፍሴን ሊያባብል ከሰማይ የመጣው የውዴ ውብ ቃል ልጄ ወዳጄ ሆይ አንቺ የኔ ሲል በኮረብታዎች ላይ መጣልኝ ሲዘል ሐዘኔን ሊያስረሳ ነፍሴን ሊያባብል የነፍሴ የውስጤ የልቤ የሚገባው ወዳጄ በቃሉ መጥቷል ወደ ደጄ ሲያንኳኳ ከፍቼ የክብርን ንጉሥ አስገባለሁ በአፉ ቃል ነፍሴን አጠግባለሁ ወዳጄ ሆይ ተነሽ ውበቴ ሆይ ነይ ክረምቱም አለፈ ብቅ አትይም ወይ አበቦች በምድር ይኸው ተገለጡ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውን ሰጡ በዓለት ንቃቃት ያለሽ እርግብ ሆይ ጊዜው ደርሷልና ነይ እንተያይ እያለ ሲያጽናናኝ ወዳጄ በቃሉ ነፍሴም ተነቃቃች እግሮቼም ዘለሉ የነፍሴ የውስጤ የልቤ የሚገባው ወዳጄ በቃሉ መጥቷል ወደ ደጄ ሲያንኳኳ ከፍቼ የክብርን ንጉሥ አስገባለሁ በአፉ ቃል ነፍሴን አጠግባለሁ የሥጋና የደሜን የልቤን ትርታ የመንፈሴን ጩኸት የነፍሴን ሙግቷ ከወንድም አብልጦ እኔን ሚጠጋጋ ወዳጅ አለኝና ለእርሱ ብቻ ላውጋ ዘልቆ የሚያረሰርስ ቃል አለና በአፉ ሥሙን እየጠራሁ ልግባ ወደ እቅፉ ቃል ብቻ ይናገር እኔም እሰማለሁ ሸክሜን ሲያራግፈው ያኔ ሰው እሆናለሁ የነፍሴ የውስጤ የልቤ የሚገባው ወዳጄ በቃሉ መጥቷል ወደ ደጄ ሲያንኳኳ ከፍቼ የክብርን ንጉሥ አስገባለሁ በአፉ ቃል ነፍሴን አጠግባለሁ