Temesgen

Temesgen

Azeb Hailu

Длительность: 4:29
Год: 2018
Скачать MP3

Текст песни

ጽድቅን እንዲያወራ ምላሴ
እንድትረካ እንድታርፍ ነፍሴ
የዋጀኸኝ አምላኬ መድህኔ
ከዚህች ዓለም አበሳ ኩነኔ

እንዳይረክስ በከንቱ ከንፈሬ
እንዳልጥለው ድንቁን ክብሬ
ዘመኔን በእጆችህ ያዝክና
አራመድከኝ በሕይወት ጐዳና

ተመስገን ተመስገን
ተመስገን ልበልህ ደግሜ
ከሃጥያት በሽታ ተፈውሼ ባንተ ታክሜ
ተመስገን ተመስገን
ተመስገን ልበልህ ደግሜ
ከሃጥያት በሽታ ተፈውሼ ባንተ ታክሜ

እንድረዳ ማዳንህን እንዳውቀው
ልቦናዬን ወዳንተ የመለስከው
እንዳያልፈኝ የሕይወቴ መና
ሕሊናዬን ለቃልህ አቀናህ

በረከሰው ዓለም የቀደስከኝ
በጽድቅ መንገድ ላይ የመራኸኝ
ከብዙዎች እኔ ተለይቼ
ዘምራለሁ መቅደስህ ገብቼ

ተመስገን ተመስገን
ተመስገን ልበልህ ደግሜ
ከሃጥያት በሽታ ተፈውሼ ባንተ ታክሜ
ተመስገን ተመስገን
ተመስገን ልበልህ ደግሜ
ከሃጥያት በሽታ ተፈውሼ ባንተ ታክሜ

አልመኝም ከእንግዲህ ወደ ውጪ
ረክቻለሁ ጌታ አንተን መርጬ
የዓለምን ከንቱነት ኮተቷን
ንቄዋለሁ ከነማንነቷ

ወስኛለሁ ልኖር አስከብሬህ
ላፈራልህ ጣፋጭ መልካም ፍሬ
ደስ እንዲልህ ሁሌ በእኔ ጌታ
እገዛለሁ ፈቅጄ በደስታ

ተመስገን ተመስገን
ተመስገን ልበልህ ደግሜ
ከሃጥያት በሽታ ተፈውሼ ባንተ ታክሜ
ተመስገን ተመስገን
ተመስገን ልበልህ ደግሜ
ከሃጥያት በሽታ ተፈውሼ ባንተ ታክሜ