ትሁን ፈቃድህ
Bereket Lemma
5:54ያደርንበት ኃጢአት ከንስሃ ጣፍጦ እግዚአብሔርን መፍራት ተንቋል አመፅ በዝቶ አንዳችን በኃጢአት ከሌላው ለመላቅ ተፎካከርን ጌታን ከቤቱ ለማራቅ ያደርንበት ኃጢአት ከንስሃ ጣፍጦ እግዚአብሔርን መፍራት ተንቋል አመፅ በዝቶ አንዳችን በኃጢአት ከሌላው ለመላቅ ተፎካከርን ጌታን ከቤቱ ለማራቅ አይታገልም ጌታ ከአፍኒንና ከፊንሃስ ጋራ ይርቃል እንጂ ከማይፈሩት ትራፊ እየሰጡ ከሚንቁት ኢካቦድ ሆኖ በሐገሪቱ በእልልታ ቢቀለጥ መንደሩ አደንድኗል አመፅ ልባቸውን እስኪሰጥ በጅራፍ ዋጋቸውን ና.. ባደባባይ ስምህ ተሰድቧል ና ና መልሰን ፊትህ ወድቀናል ና.... የተወሰደው ክብር ይመለስ ና ና አንተ ቆይልን ሚሄደው ይሂድ ሙሽራው እያለ ሎሌው ደምቆ ነውር የማይፈራ ምህረቱን ተለማምዶ ሙሽሪትም ደጇን ለሌላው ከፍታ በአላፊው አግዳሚው ጨረሰች ዘይቷን የለበትም ጌታ በምስባኩ በተዘጋዘጀው በስሙ ይሰበካል እንጂ የሰው ዝና ባሪያው ከጌታው ልቋልና አይጠራም ኢየሱስ በመድረኩ አይነገርም ከቶ ትምህርቱ ይሰበካል እንጂ ታምራቱ ለንግድ የሚሆን ጥራዝ ጥቅሱ ይኑርልን ጌታ በቤቱ ይሰንብት ለርስቱ ሚፈልገው አለ ከነፍሱ የማይኖር ያለ እሱ ባይተዋር አናርገው አንግፋው ይኑርልን ጌታ ዝም ማለቱን አንናቅ ምህረቱ ሲበዛ ላይ ላያችን ሲታይ ጣዖት ተፀያፊ በቤተ መቅደስ ግን ከእግዜር እጅ ዘራፊ በድፍረት ልምምድ ጌታን ስንጋፋ የምህረት ደጁን እግዜር እንዳይዘጋ ና.. ባደባባይ ስምህ ተሰድቧል ና ና መልሰን ፊትህ ወድቀናል ና.... የተወሰደው ክብር ይመለስ ና ና አንተ ቆይልን ሚሄድዉ ይሂድ