Edmeye Betih Yilek
Betty Tezera
አልዋሽህም ልቤን ታያለህና አልዋሽህም የልብ አምላክ ነህ እላለሁ እርቦኛል በእውነት ፊትህ ላምልክህ ይርዳኝና መንፈስህ ከስሬ ደርቼ ድሪቶዬን ከላይ ብለብሰው የፀዳውን ሰው እንደው የሚያየው ፊቴ ፊቴን እከልላለሁ ገበናዬን ግን አንተ አትዋሽም አትታለል ዓይንህ ዘልቆ ልብን ያያል ዓይንህ ዘልቆ ልብን ያያል የቀድሞውን ፍቅር አጣሁት ፈላልጌ ኧረ እኔስ ፈራሁኝ ወዴት ነው ማደጊያዬ ኧረ እኔስ ፈራሁኝ ወዴት ነው እግዚአብሔር ደጅ እንዳልጠናሁኝ ዛሬማ ላፍታ እንኳ አቅም አጣሁ ናፈቀኝ የጥንቱ ክብር ናፈቀኝ ቤቴ የነበረ ናፈቀኝ ኦ እግዚአብሔር ናፈቀኝ ረሃቤ ትጋቴ ናፈቀኝ ትንሿ አንዷ ሀሳቤ ናፈቀኝ ያ ፀሎቴ የተገለጠው ማንነቴ ይኸው በፊትህ መድኃኒቴ አቅም አጣሁኝ አግዘኝ ያዘኝ ኃይልህን አልብሰኝ ለአንተ ያለኝ ፍቅር ትኩስ የማይበርድ በልቤ የሚኖር ሁል ጊዜ የሚነድ መስሎኝ እንዳልነበር በልጅነቴ ወራት ራሴን አገኘሁት ልምድ ሆኖብኝ ቀላት ቤቴን አዘረፍኩት ከፍቼ ለጠላት ናፈቀኝ ለቃልህ ያለኝ ቦታ ናፈቀኝ ያንን የእሺታ ናፈቀኝ ኦ እርዳኝ ጌታ ናፈቀኝ ለአንተ ያለኝ ክብር ናፈቀኝ ሥምህ ሲነገር ናፈቀኝ ኦ እግዚአብሔር የተገለጠው ማንነቴ ይኸው በፊትህ መድኃኒቴ አቅም አጣሁኝ አግዘኝ ያዘኝ ኃይልህን አልብሰኝ ይልቅ ይልቅ ይቅርብኝ ልመልስ ወደ ልብህ ወደ ሀሳብህ ልድረስ ልሸከመው የመስቀልህን ፍቅር ተመልሼ ወደ ኋላ አልመልከት አድስልኝ የቀድሞውን ናፍቆት ሆኖ ምኞት ሆኖ እንዳይቀር ሰምቼ አንተን እንዳፈራበት ለም አድርገው የልቤን መሬት