Anbesaw
Daniel Amdemichael
5:39አዝ: - አሁንማ ፤ ብርሃንህ ፡ በእኔ ፡ ደምቋል መከራም ፡ ከኔ ፡ ርቋል ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ምን ፡ እላለሁ ፤ ስምክን ፡ ከማክበር ፡ በቀር ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ልናገር ፡ ስላደረክልኝ ፡ ነገር (፪x) በዓለም ፡ ላይ ፡ ከሚታየው ፡ ከአልማዝ ፡ ከወርቅ ፡ ከዕንቁ የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ይበልጣል ፡ አባት ፡ ነህ ፡ ለተጠቁ ምስክር ፡ ነኝ ፡ ለዚህ ፡ እኔ ፡ ማዳንህን ፡ አይቻለሁ ያባትነት ፡ ፍቅርህን ፡ ምህረትህን ፡ እዘምራለሁ ተመስገን ፡ እያልኩ ፡ ላክብር ፡ ስምህን በእርግጥ ፡ ስላየሁ ፡ ጌትነትህን በአማረ ፡ ዜማ ፡ ቅኔ ፡ ውዳሴ ልዑል ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ያክብርህ ፡ ነፍሴ አዝ: - አሁንማ ፤ ብርሃንህ ፡ በእኔ ፡ ደምቋል መከራም ፡ ከኔ ፡ ርቋል ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ምን ፡ እላለሁ ፤ ስምክን ፡ ከማክበር ፡ በቀር ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ልናገር ፡ ስላደረክልኝ ፡ ነገር (፪x) ማረፊያ ፡ ለምስኪኑ ፡ ማጠጊያ ፡ ለደሃው ፡ ሰው ይህንን ፡ አይቻለሁ ፡ እንባውን ፡ ስታብሰው ደግ ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ግሩም ፡ በምክርህ ምህረትህ ፡ አይለካም ፡ ወደር ፡ የለው ፡ ለፍቅርህ አሉ ፡ ብዙዎች ፡ የታደጋቸው ስምህን ፡ የሚጠሩ ፡ በምሥጋናቸው እያደነቁ ፡ ግሩም ፡ ስምህን ይዘምራሉ ፡ ጌትነትህን አዝ: - አሁንማ ፤ ብርሃንህ ፡ በእኔ ፡ ደምቋል መከራም ፡ ከኔ ፡ ርቋል ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ምን ፡ እላለሁ ፤ ስምክን ፡ ከማክበር ፡ በቀር ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ልናገር ፡ ስላደረክልኝ ፡ ነገር (፪x)