Notice: file_put_contents(): Write of 661 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Daniel Amdemichael - Besemay Zufanu | Скачать MP3 бесплатно
Besemay Zufanu

Besemay Zufanu

Daniel Amdemichael

Альбом: Yesew Eje Yelelebet
Длительность: 5:16
Год: 2013
Скачать MP3

Текст песни

በሠማይ ዙፋኑ በመቅደሱ ያለው
የፍጥረት ፈጣሪ እግዚአብሔር ድንቅ ነው
ዓይኑ እንዳየ አይፈርድ ጆሮው እንደሰማ
በምክሩ ትክክል ታማኝ ነው እርሱማ
ልብን ኩላሊትን የሚመረምረው
እንደሰው ያይደለ እግዚአብሔር ጻዲቅ ነው

የሚያድን ነው ደግሞም የሚራራ
አቤቱ ማረኝ ላለ
ወደ እርሱ ለተጠጋ
ውድ ልጁ በመረቀልን በር
ወደ እርሱ መግባት አለ አሄ
ታላቅ ስሙ ይክበር

በምክሩ ጠቢብ ፍቅሩ የላቀ
በልጆቹ ላይ ግርማው የደመቀ
ምሥጋና ሞላ በማደሪያው ላይ
በመንጋው መልካም ማዳኑን ሲታይ

በሠማይ ዙፋኑ በመቅደሱ ያለው
የፍጥረት ፈጣሪ እግዚአብሔር ድንቅ ነው
ዓይኑ እንዳየ አይፈርድ ጆሮው እንደሰማ
በምክሩ ትክክል ታማኝ ነው እርሱማ
ልብን ኩላሊትን የሚመረምረው
እንደሰው ያይደለ እግዚአብሔር ጻዲቅ ነው

ታናሹን ሰው ለክብር የሚያበቃው
የዳዊት የሙሴ አምላክ አሄ ለትሁቱ ጠበቃ
የወህኒውን መዝጊያ የሚሰብር
ለባሪያዎቹ ፈራጅ የሚሆን ሞገስ ክብር

አቢት እግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነው
በመልካም ዜማ እስቲ እናምልከው
ክብሩ ይታወጅ በቤቱ መድረክ
የዘለዓለሙ አምላክ ይባረክ

በሠማይ ዙፋኑ በመቅደሱ ያለው
የፍጥረት ፈጣሪ እግዚአብሔር ድንቅ ነው
ዓይኑ እንዳየ አይፈርድ ጆሮው እንደሰማ
በምክሩ ትክክል ታማኝ ነው እርሱማ
ልብን ኩላሊትንየሚመረምረው
እንደሰው ያይደለ እግዚአብሔር ጻዲቅ ነው

ተራሮችን ከላይ የሚያጠጣ
ለጻድቅ ለሃጥኡ አሄ ፀሐይን የሚያወጣ
ደረቁን ምድር የሚያለመልመው
ለታናሹ ሰው ብርታት እህ ሞገስ የሚሰጠው

ምሥጋናን ያምጡ ለእርሱ ያደሩ
በመንፈሱ ኃይል እየዘመሩ
የቤቱ ካህናት ምስክሮቹ
ስሙን ያክብሩ ታማኝ ባሮቹ

በሠማይ ዙፋኑ በመቅደሱ ያለው
የፍጥረት ፈጣሪ እግዚአብሔር ድንቅ ነው