Notice: file_put_contents(): Write of 653 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Daniel Amdemichael - Dingayu Libe | Скачать MP3 бесплатно
Dingayu Libe

Dingayu Libe

Daniel Amdemichael

Альбом: Selam Lemidrachin
Длительность: 4:53
Год: 2022
Скачать MP3

Текст песни

ድንጋዩ ልቤ ጠጣሩ ልቤ
መች በቀላሉ ታዛዥ ነበረ
የአንተ ፍቅር ግን ውስጤን ሰበረ
ተረትቻለሁ ተሸንፌያለሁ
ኢየሱሴ ለአንተ እጅ ሰጥቻለሁ
ዛሬ በፍቅርህ ተማርኬያለሁ

ብዙ የከበሩ በምድር ላይ ሞልተው
ታላቅ ነኝ ባዩን ልታሳፍረው
እኔን መረጥከኝ ዓሣ አጥማጁን ሰው
ኧረ ልዩ ነው ኢየሱሴ ፍቅርህ
ሀብታም ደሀ አይል አመራረጥህ
ለእኔም ደረሰኝ ድንቅ ማዳንህ

ድንጋዩ ልቤ ጠጣሩ ልቤ
መች በቀላሉ ታዛዥ ነበረ
የአንተ ፍቅር ግን ውስጤን ሰበረ
ተረትቻለሁ ተሸንፌያለሁ
ኢየሱሴ ለአንተ እጅ ሰጥቻለሁ
ዛሬ በፍቅርህ ተማርኬያለሁ

ለያልፍለት ለዚህ ሥጋዬ
ቀን ከሌት ስደክም መረቤን ጥዬ
ምንም ላላገኝ በድካም ዝዬ
አንተ ግን መጥተህ ተዓምርን ሰራህ
መላው ሕይወቴን መገረም ሞላህ
ሥሜን ተግባሬን ኑሮዬን ቀየርክ

ድንጋዩ ልቤ ጠጣሩ ልቤ
መች በቀላሉ ታዛዥ ነበረ
የአንተ ፍቅር ግን ውስጤን ሰበረ
ተረትቻለሁ ተሸንፌያለሁ
ኢየሱሴ ለአንተ እጅ ሰጥቻለሁ
ዛሬ በፍቅርህ ተማርኬያለሁ

ከኃላዬ ና ወድጄሃለሁ
ለማዳን ስራ መርጬሃለሁ
ሰዎችን አጥማጅ አደርግሃለሁ
አልከኝ ጌታዬ እኔም ተረታሁ
ከልብ ወደድኩህ ህይወቴን ሰጠሁ
እስከ ዘላለም አመልክሃለሁ

ድንጋዩ ልቤ ጠጣሩ ልቤ
መች በቀላሉ ታዛዥ ነበረ
የአንተ ፍቅር ግን ውስጤን ሰበረ
ተረትቻለሁ ተሸንፌያለሁ
ኢየሱሴ ለአንተ እጅ ሰጥቻለሁ
ዛሬ በፍቅርህ ተማርኬያለሁ

የዋህነትህ ትህትናህ ሳበኝ
በኃይል በጉልበት አላስገደድከኝ
ድንቅ ፍቅርህ ነው ያንበረከከኝ
ልከተል ወሰንኩ ቸሩ ጌታዬ
በነገር ሁሉ አንተን ታምኜ
መረብ ታንኳዬን ሁሉንም ጥዬ