Notice: file_put_contents(): Write of 637 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Daniel Amdemichael - Ersunew | Скачать MP3 бесплатно
Ersunew

Ersunew

Daniel Amdemichael

Альбом: Selam Vol. 5
Длительность: 7:04
Год: 2008
Скачать MP3

Текст песни

አዝ: - እርሱ ፡ ነው ፡ የደሃ ፡ ደግ ፡ ወዳጅ ፡ የባልቴቶች ፡ ዳኛ
ድሃውን ፡ ምግቡን ፡ የሚያጐርሰው ፡ ጾሙን ፡ እንዳይተኛ
የተጣለውን ፡ አይቶ ፡ የማያልፍ ፡ ከትቢያ ፡ ሚያነሳው
እሩህሩህ ፡ ነው ፡ ጌታ

ወዳጅ ፡ ዘመድ ፡ ገፍቶ ፡ ላራቀው
ኢየሱስ ፡ ይደርስለታል ፡ አምላኬ ፡ ይደርስለታል
ልቡን ፡ ሃዘን ፡ በጣም ፡ ለጐዳው
መጽናናት ፡ ይሆንለታል (፪x)
ማረፊያ ፡ ነው ፡ ለተጣለው ፡ ሰው
አይተናል ፡ እንባውን ፡ ሲያብሰው (፪x)
ከቅዱሳን ፡ መሃል ፡ ሲያቆመው
ሲያከብረው ፡ ሞገስ ፡ ሲሆነው (፪x)

ድንቅ ፡ ፍቅሩን ፡ አይቻለሁ ፡ መጠጊያ ፡ ሆኖኝ ፡ መድህኔ
ወጀቡ ፡ እንዳያንገላታኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ሲቆም ፡ ከጐኔ
ባወራው ፡ ቃላት ፡ ያጥረኛል ፡ ብቆጥረው ፡ የእርሱን ፡ ውለታ
እንዲያው ፡ ላመስግነው ፡ እንጂ ፡ በጠዋት ፡ ደግሞም ፡ በማታ

አዝ: - እርሱ ፡ ነው ፡ የደሃ ፡ ደግ ፡ ወዳጅ ፡ የባልቴቶች ፡ ዳኛ
ድሃውን ፡ ምግቡን ፡ የሚያጐርሰው ፡ ጾሙን ፡ እንዳይተኛ
የተጣለውን ፡ አይቶ ፡ የማያልፍ ፡ ከትቢያ ፡ ሚያነሳው
እሩህሩህ ፡ ነው ፡ ጌታ

ቸርነቱን ፡ ያውራ ፡ የቀመሰው ፡ ይዘምር ፡ እንደኔ ፡ ያለው (፪x)
ማቁን ፡ ቀዶ ፡ ደስታ ፡ ያስታጠቀው ፡ ምህረቱ ፡ ሰው ፡ ያደረገው (፪x)
ምንም ፡ የለም ፡ የኔ ፡ የምለው ፡ አንድ ፡ ሁለት ፡ ብዬ ፡ ምቆጥረው (፪x)
ጽድቄም ፡ ቅድሳዬ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ በመስቀል ፡ ለእኔ ፡ የሞተው
በመስቀል ፡ ሁሉን ፡ የሰራው

ሁሉም ፡ ነገር ፡ ተፈጸመ ፡ ተፈጸመ ፡ ያለ ፡ ለታ
አሮጌው ፡ ማንነት ፡ አልፎ ፡ በአዲሱ ፡ ሕይወት ፡ ተተካ
አፋቸው ፡ ምሥጋና ፡ ሰማ ፡ ኢሄ ፡ ሚስጥር ፡ የገባቸው
በትንሳኤው ፡ የለበሱት ፡ ኢየሱስ ፡ ሁኖ ፡ ኑሯቸው

ለእኔስ ፡ ብርሃን ፡ በርታልኛለች ፡ ከሰማይ ፡ ድምቅ ፡ እያለች (፪x)
ጨለማውን ፡ እየገፈፈች ፡ የጌታን ፡ ጽድቅ ፡ እያሳየች ፤ የአምላኬን ፡ ጽድቅ ፡ እያሳየች
የመስቀሉ ፡ ስራ ፡ ስገለጥ ፡ በሕይወቴ ፡ እውነት ፡ ሲበራ
አስታረቀኝ ፡ ከአምላኬ ፡ ጋራ ፡ ይዘመር ፡ ይሄስ ፡ ይወራ (፪x)
ምሰጠው ፡ አንዳች ፡ የእልኝም ፡ ማን ፡ ልበለው ፡ መድሃኒቴን
ምሥጋናን ፡ ሰላም ፡ ደስታን ፡ እርካታን ፡ ሞልቷል ፡ ሕይወቴን
ልቀኝለት ፡ አዲስ ፡ ቅኔን ፡ ይበልጣል ፡ እርሱ ፡ የፈቀደው
ለሥሙ ፡ ምሥጋና ፡ ይሁን ፡ ለኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ለሆነው

አዝ: - እርሱ ፡ ነው ፡ የደሃ ፡ ደግ ፡ ወዳጅ ፡ የባልቴቶች ፡ ዳኛ
ድሃውን ፡ ምግቡን ፡ የሚያጐርሰው ፡ ጾሙን ፡ እንዳይተኛ
የተጣለውን ፡ አይቶ ፡ የማያልፍ ፡ ከትቢያ ፡ ሚያነሳው
እሩህሩህ ፡ ነው ፡ ጌታ