Sinegam
Daniel Amdemichael
4:54ያ ፡ የጥንቱ ፡ ፍቅራችን ፡ መሃላችን ፡ የታለ ኀጢአታችን ፡ በዝቶ ፡ ጥላቻን ፡ አበቀለ ከአንተ ፡ ያልተቀበልነው ፡ ያልሰጠኀን ፡ ምን ፡ አለ ሁሉም ፡ ተረስቶ ፡ ዛሬ ፡ ትዕቢታችን ፡ ከፍ ፡ አለ አዝ: - ኢየሱስ (፪x) ፡ በማስተዋል ፡ ሙላን ፡ በማስተዋል (፪x) ኀጢአት ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ አይሆንም ፡ ለማጥ ሞትን ፡ ይወልዳል ፡ ለሕይወት ፡ ጥፋት ደሙ ፡ ያላጠበው ፡ ያልተመለሰ እናስብ ፡ እንጂ ፡ ከየት ፡ ደረሰ ምክንያት ፡ አንደርድር ፡ ለድካማችን ከሞት ፡ ያድናል ፡ መመለሳችን ኑሯችን ፡ ከንቱ ፡ ከእውነት ፡ የሚጣረስ ንሰሃ ፡ እንግባ ፡ ሳናለባብስ ቦታ ፡ አጥቶ ፡ ቅድስና ፡ ኀጢአት ፡ ተሞልቷል ፡ ቤቱ ሁሉም ፡ አንተን ፡ አልፈራም ፡ ይስታል ፡ በአንደበቱ የጥበብ ፡ መጄሪያው ፡ አንተን ፡ መፍራቱ ፡ ጠፍቶ ሁሉ ፡ እንዳሻው ፡ ይሄዳል ፡ ቤቱ ፡ በአመጽ ፡ ትሞልቶ አዝ: - ኢየሱስ (፪x) ፡ በማስተዋል ፡ ሙላን ፡ በማስተዋል (፪x) ከየት ፡ ተማርነው ፡ ወንድምን ፡ መጥላት ከነብያት ፡ ነው ፡ ወይንስ ፡ ከሓዋርያት የቀደሙትን ፡ የምናውቃቸው ፡ በመልካም ፡ ፍቅር ፡ በጸኦታቸው ለእውነት ፡ እንኑር ፡ ከቶ ፡ አንገበዝ ደሙ ፡ ያነጻናል ፡ ትሎ ፡ እንመለስ የሰማይ ፡ ጥበበ ፡ የላይኛይቱን ከአምላክ ፡ እንለምን ፡ ይሰማል ፡ ሁሉን (፪x)