Amesegnalehu
Daniel Amdemichael
8:06ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ የሕይወቴ ፡ ጌታ ፡ ኦሆ ጽኑ ፡ መሰረቴ ፡ የነፍሴ ፡ መከታ የራራልኝ ፡ ቀድሞ ፡ በፍቅሩ ፡ የሳበኝ ጨለማዬን ፡ ገፎጭ ፡ በብርሃን ፡ ያኖረኝ ቅኔን ፡ ጨመረልኝ ፡ በአፌ ለክብሩ ፡ እንድዘምር ፡ ከልቤ ምሥጋናውን ፡ ደግሞ ፡ እንዳወራ አብሬ ፡ እንዳመልከው ፡ ከቅዱሳን ፡ ጋራ ከአሪያም ፡ ወረደ ፡ መንፈሱ ልቤን ፡ አደረገው ፡ መቅደሱ አቤት ፡ የአምላክ ፡ ፍቅር ፡ ምህረቱ ኢኸው ፡ ልጅ ፡ አደረገኝ ፡ እንድኖር ፡ በቤቱ ከቁጥር ፡ ያለፈ ፡ ቸርነት ፡ ሠማያዊ ፡ ፀጋን ፡ አሄ አምላኬ ፡ ሰጥቶኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ሕይወት ማዳኑን ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ገለጠ በደሙ ፡ ቀደሰኝ ፡ አሄ ኢየሱስ ፡ ሕይወቴን ፡ መልካም ፡ አደረገ ምድር ፡ እልል ፡ ትበል ፡ ለንጉሡ ሠማይም ፡ ያጨብጭብ ፡ ለቅዱሱ ሁሉንም ፡ በኃይሉ ፡ የፈጠረው የዘለዓለም ፡ ዓለም ፡ መንግሥት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው ማዳኑን ፡ ልዘምር ፡ ከፍ ፡ ላድርገው ከምርጦቹ ፡ ጋራ ፡ ላመስግነው የጠለቀ ፡ ፍቅሩንም ፡ ልናገር ከሠማይ ፡ በምድር ፡ ታላቅ ፡ ስሙ ፡ ይክበር ፍቅሩን ፡ አፈሰሰ ፡ ማዳኑን ፡ ገለጠ ፡ እህ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቶ ፡ ምህረቱን ፡ አወጀ እርሱን ፡ ያመነች ፡ ነፍ ፡ በሕይወት ፡ ትኖር ፡ ዘንድ ቤዛ ፡ ለዓለሙ ፡ ሆነ ፡ የኀጢአት ፡ መሥዋዕት ሞትን ፡ ያሸነፈ ፡ ግድለኛ ፡ ማኅተሙን ፡ የፈታ ፡ ኃይለኛ የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ አንበሳ ፡ ምሥጋና ፡ የሚገባው ፡ ክብርና ፡ ሙገሳ የጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ ግርማዊ ፡ መንግሥት ፡ ከላይ ፡ ነው ፡ ሠማያዊ ፍጥረት ፡ በመገዛት ፡ የሚያከብረው ፡ የዓለም ፡ መድሃኒት ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው አቻ ፡ ይገኝለት ፡ መውደዱ ፡ አቤት ፡ የአምላክ ፡ ፍቅር ፡ አሄ ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ምህረት ፡ ተገዝቶ ፡ አሄ ምክሩ ፡ ከሰው ፡ ጥበብ ፡ የላቀ ማስተዋሉ ፡ ረቂቅ ፡ አሄ ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታችን ፡ በክብር ፡ የደመቀ ሃሌሉያ ፡ ልበል ፡ ላመስግነው ኃይልና ፡ ጥበብም ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው ሃሴት ፡ ታደርጋለች ፡ ዘወትር ፡ ነፍሴ ሁሌ ፡ እያቀረበች ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ ክብር ፡ ለሚገባው ፡ ክብር ፡ ይሁን በዙፋኑ ፡ ላለው ፡ ኦ ፡ ልዘምር ለአማልክት ፡ አምላክ ፡ ይሁን ፡ ስግደት በሠማይ ፡ በምድር ፡ ኃይልና ፡ በረከት ሃሌሉያ ፡ ልበል ፡ ላመስግነው ኃይልና ፡ ጥበብም ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው ሃሴት ፡ ታደርጋለች ፡ ዘወትር ፡ ነፍሴ ሁሌ ፡ እያቀረበች ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ ክብር ፡ ለሚገባው ፡ ክብር ፡ ይሁን በዙፋኑ ፡ ላለው ፡ ኦ ፡ ልዘምር ለአማልክት ፡ አምላክ ፡ ይሁን ፡ ስግደት በሠማይ ፡ በምድር ፡ ኃይልና ፡ በረከት "አምልኮና ፡ ስግደት ፡ ይሁንለት አምልኮ ፡ ስግደት ፡ ይሁንለት ለንጉሡ ፡ ለንጉሡ"