Notice: file_put_contents(): Write of 655 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Daniel Amdemichael - Meche Eresahu | Скачать MP3 бесплатно
Meche Eresahu

Meche Eresahu

Daniel Amdemichael

Альбом: Selam Lemidrachin
Длительность: 4:59
Год: 2022
Скачать MP3

Текст песни

አዝ፦ መች እረሳሁ? መች ዘነጋሁ?
ሁሉንም አስታውሳለሁ
ከሕጻንነቴ ጀምሮ ስትመራኝ
ማዳንህን አይቻለሁ
እጆቼን ላንሳ ላክብርህ
ምሥጋናዬን ተቀበለው
ብቻውን ተዓምር የሚያደርግ የሚሠራ
ኧረ እንደርሱ ያለ ማነው

የራራልኝ በድካሜ
ኃይል የሆነልኝ አቅሜ
ጐኔ ቆሞ ያበረታኝ
ማን ነበረ ከአንተ በላይ

አዝ፦ መች እረሳሁ? መች ዘነጋሁ?
ሁሉንም አስታውሳለሁ
ከሕጻንነቴ ጀምሮ ስትመራኝ
ማዳንህን አይቻለሁ
እጆቼን ላንሳ ላክብርህ
ምሥጋናዬን ተቀበለው
ብቻውን ተዓምር የሚያደርግ የሚሠራ
ኧረ እንደርሱ ያለ ማነው

ከንፈሮቼን ቀባሃቸው
ጠላቶቼ እያየ ዓይናቸው
ዝማሬ በአፌ ጨምረሃል
አመልክህ ዘንድ ይገባኛል

አዝ፦ መች እረሳሁ? መች ዘነጋሁ
ሁሉንም አስታውሳለሁ
ከሕጻንነቴ ጀምሮ ስትመራኝ
ማዳንህን አይቻለሁ
እጆቼን ላንሳ ላክብርህ
ምሥጋናዬን ተቀበለው
ብቻውን ተዓምር የሚያደርግ የሚሠራ
ኧረ እንደርሱ ያለ ማነው

ሁሉም አልፎ እዚህ መድረሴ
በአንተ እንጂ መች በራሴ
ክብር ለአንተ እሰጣለሁ
ሁልጊዜ እዘምራለሁ

አዝ፦ መች እረሳሁ? መች ዘነጋሁ
ሁሉንም አስታውሳለሁ
ከሕጻንነቴ ጀምሮ ስትመራኝ
ማዳንህን አይቻለሁ
እጆቼን ላንሳ ላክብርህ
ምሥጋናዬን ተቀበለው
ብቻውን ተዓምር የሚያደርግ የሚሠራ
ኧረ እንደርሱ ያለ ማነመ

ልቤን ፍፁም ደስታ ሞላው
የአንተ መሆኔን ሳስበው
ብዙ ሰላም በዝቶልኛል
ከአንተ እጅ ማን ያወጣኛል