Alefewalehu
Daniel Amdemichael
5:33ሰላም ፡ ነው ፡ ከጌታ ፡ ጋር ፡ ውሎ ፡ ማደር መልካም ፡ አምላክ ፡ በእቅፉ ፡ ይዞኛል አልሻም ፡ ምንም ፡ ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ ወዳጅ ፡ የለም ፍቅሩ ፡ ከጨለማ ፡ ስቦ ፡ አውጥቶኛል ሁሉን ፡ በሚችለው ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አድራለሁ ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ እተማመናለሁ ጌታ ፡ መልካም ፡ አምላክ ፡ ነው (ኦሆሆሆ) ጌታ ፡ መልካም ፡ አምላክ ፡ ነው ሰላምን ፡ ይሿታል ፡ በወርቅ ፡ በብር ፡ ሊያገኟት በዓልማዝ ፡ በዕንቁ ፡ አትመጣም ፡ ምን ፡ ያህል ፡ ቢያፈሱላት ከእግዚአብሔር ፡ የታረቀ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የዘየደ በአምላክ ፡ ሰላም ፡ ይጠግባል ፡ በመንገዱ ፡ የሄደ (፪x) በፈቃዱ ፡ የሄደ (፪x) ሰላም ፡ ነው ፡ ከጌታ ፡ ጋር ፡ ውሎ ፡ ማደር መልካም ፡ አምላክ ፡ በእቅፉ ፡ ይዞኛል አልሻም ፡ ምንም ፡ ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ ወዳጅ ፡ የለም ፍቅሩ ፡ ከጨለማ ፡ ስቦ ፡ አውጥቶኛል ሁሉን ፡ በሚችለው ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አድራለሁ ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ እተማመናለሁ ጌታ ፡ መልካም ፡ አምላክ ፡ ነው (ኦሆሆሆ) ጌታ ፡ መልካም ፡ አምላክ ፡ ነው ሆድ ፡ በእንጀራ ፡ ቢሞላ ፡ ገላም ፡ ምርጡን ፡ ቢለብስ የነፍስ ፡ ጐዶሎ ፡ አይሞላም ፡ ሰው ፡ ሁሉን ፡ ቢያግበሰብስ ሰማያዊው ፡ ደስታ ፡ አምላክ ፡ ከላይ ፡ የላከው ሰላም ፡ ማለት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ተሰፍሮ ፡ የማይለካው (፪x) ሰው ፡ ዓለምን ፡ አትርፎ ፡ ውድ ፡ ነፍሱን ፡ ቢያዶላት ከቶ ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል ፡ መጨረሻው ፡ ነው ፡ ጥፋት ብሩክ ፡ ትሁን ፡ ያቺ ፡ ቀን ፡ ወንጌል ፡ የሰማሁባት በክርስቶስ ፡ መስቀል ፡ ስራ ፡ ከአምላክ ፡ ጋር ፡ የታረቅኩባት (፪x) ወንጌል ፡ የሰማሁባት ፡ አሄ ፡ ሰላም ፡ ያገኘሁባት ሰላም ፡ ነው ፡ ከጌታ ፡ ጋር ፡ ውሎ ፡ ማደር መልካም ፡ አምላክ ፡ በእቅፉ ፡ ይዞኛል አልሻም ፡ ምንም ፡ ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ ወዳጅ ፡ የለም ፍቅሩ ፡ ከጨለማ ፡ ስቦ ፡ አውጥቶኛል ሁሉን ፡ በሚችለው ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ አድራለሁ ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ እተማመናለሁ ጌታ ፡ መልካም ፡ አምላክ ፡ ነው (ኦሆሆሆ) ጌታ ፡ መልካም ፡ አምላክ ፡ ነው