Zelalem Ayitefam
Dawit Getachew Abreham
5:06ድሮ ፡ ገና ፡ ከማህፀን ፡ ሳለሁ ፡ በእናቴ ፡ ሆድ በሥም ፡ ጠርተህ ፡ የለየኸኝ ፡ ክፉን ፡ ደጉን ፡ ሳላውቅ የአንተ ፡ ክብር ፡ መገለጫ ፡ እንድሆን ፡ በቤትህ ከነኃጢአቴ ፡ የመረጥከኝ ፡ ለአንተ ፡ እንድኖርልህ በሰጠኸኝ ፡ መንገድ ፡ ስሄድ ፡ ባሰብክልኝ ፡ ስፍራ እንዳልገኝ ፡ ሳሳዝንህ ፡ ቸል ፡ ብዬ ፡ ሳልሰማህ ዛሬ ፡ በቀን ፡ ለምንሃለሁ ፡ ኃይልህ ፡ እንዲረዳኝ በመክሊቴ ፡ ብዙ ፡ አትርፌ ፡ አንተን ፡ ደስ ፡ እንዳሰኝ አዝ:- ኃይልህ ፡ ይርዳኝ ፡ ለምናለው እንድትረዳኝም ፡ አምናለሁ መልካም ፡ ነገር ፡ ያደረኩኝ ፡ መስሎኝ ሳሳዝንህ ፡ እንዳልገኝ ስመላለስ ፡ በዚህች ፡ ምድር ፡ ሳገለግል ፡ አንተን የማልኖረውን ፡ አውርቼ ፡ የተጣልኩ ፡ እንዳልሆን እንዳታልፈኝ ፡ እፈራለሁ ፡ በምትመጣበት ፡ ቀን ሕይወቴም ፡ አንተን ፡ ያክብርህ ፡ አፌ ፡ ብቻ ፡ ሳይሆን ክብርህን ፡ አሳየኝ ፡ የአንተን ፡ ማንነት ቅዱሱን ፡ መንፈስህን ፡ ሚመራኝ ፡ ወደ ፡ እውነት እኔ ፡ ደካማና ፡ ኃጢአተኛ ፡ ሰው ፡ ነኝ ሃይልህ ፡ ግን ፡ ከረዳኝ ፡ ከእግሬ ፡ እቆማለሁ አዝ:- ኃይልህ ፡ ይርዳኝ ፡ ለምናለው እንድትረዳኝም ፡ አምናለሁ መልካም ፡ ነገር ፡ ያደረኩኝ ፡ መስሎኝ ሳሳዝንህ ፡ እንዳልገኝ ቀድመህ ፡ ውጣ ፡ በሕይወቴ ልከተልህ ፡ ቸሩ ፡ አባቴ አንተ ፡ ቀድመኀኝ ፡ ካልወጣህ እኔ ፡ ብሮጥ ፡ ምን ፡ ላመጣ ለምንሃለሁ ፡ ጌታ ለምንሃለሁ ፡ ኢየሱስ ኃይልህ ፡ ይርዳኝ ፡ ጌታ