Notice: file_put_contents(): Write of 639 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Dawit Mellesse - Endalsh | Скачать MP3 бесплатно
Endalsh

Endalsh

Dawit Mellesse

Длительность: 4:34
Год: 2025
Скачать MP3

Текст песни

እንዳልሽ

ወዴት ነው ያለሽው ያለሽበት ሀገር
መኖር እንደማልችል እያወቅሽ ካንች በቀር
ያለፈውን ትተሽ ብቻ ነይ እንተያይ
ጥፋተኛ ልባል  ይሳበብ በኔ ላይ
ይሁን ብያለሁ  ባልሽውእስማማለሁ
ይሁን ብያለሁ  ምንስ አደርጋለሁ

ነይልኝ ስልሽ ናፍቀሽኛል
ስትሄጂ ባዶ አካል አርገሽኛል
ከፍቅርሽ በቀር ልቤስ ገብቶ
ምን ጉዳይ ሊቀመጥ አንቺን ገፍቶ

እያነሳሁሽ ጠዋት ማታ
ይቅርታ ስል ሆኜ ባንቺ ቦታ
የኔንም መልካም ካልዘነጋሽ
የምትይው ይሁን ይሁን እንዳልሽ

እንዳልሽ ብያለሁ እንዳልሽ
ይሁን ብያለሁ እንዳልሽ
የእኔስ ቢቀር ይሻላል ሆዴ አንቺን ከማስከፋሽ

እንዳልሽ ብያለሁ እንዳልሽ
ይሁን ብያለሁ እንዳልሽ
የእኔስ ቢቀር ይሻላል እኔ አንቺንስ ከማጣሽ

ወዴት ነው ያለሽው ያለሽበት ሀገር
መኖር እንደማልችል እያወቅሽ ካንች በቀር
ያለፈውን ትተሽ ብቻ ነይ እንተያይ
ጥፋተኛ ልባል  ይሳበብ በኔ ላይ
ይሁን ብያለሁ  ባልሽው እስማማለሁ
ይሁን ብያለሁ  ምንስ አደርጋለሁ

ስትሄጂ ርቀሽ ሳይኖር ከሳሽ
ስትጠፊ ባገሩ አንቺን መላሽ
አጥቼሽ አንዲህ ከምቸገር
እስማማለሁ ይሁን ባልሽው ነገር

ደግሞስ ያብሮነት አንድ አካሉ
ማለፍ አይደለም ወይ መቻቻሉ
ፍቅር ነውና አማላጄ
አንቺ እንዳልሽው ይሁን ነይ ወዳጄ

እንዳልሽ ብያለሁ እንዳልሽ
ይሁን ብያለሁ እንዳልሽ
እኔስ ቢቀር ይሻላል ሆዴ አንቺን ከማስከፋሽ

እንዳልሽ ብያለሁ እንዳልሽ
ይሁን ብያለሁ እንዳልሽ
የእኔስ ቢቀር ይሻላል እኔ አንቺንስ ከማጣሽ