Yelibe Zema
Dibekulu
4:25የጥንቱን ታሪኳን ስመራመርበት ጥልቅ እውቀት አገኘሁ ፍቅሯን ስማርበት ገና ወጣት ሳለች እንቡጥ ጽጌረዳ ፍቅር አስተምራለች ያቺ ሰለስቴ አይዳ የግብፁን ጦረኛ ጀግናው ራዳሚስ በመልኳ ተጠልፎ ጥሎት የሷ ቀሚስ ደምግባቷን ወዶ ሀገሩን ቢከዳ አይዞህ አለሁልህ ብላዋለች አይዳ ገራችው ሃይሉን ገራችው በፍቅር አስተማረችው እየራራችለት እሱንም አራርታው ህዝቧን ነፃ አወጣች በውበት እረታው አሸነፈኝ ብላ ቂምም ሳትይዝበት ፈቀደች በፍቅር ልቧን እንዲያዝበት ሰለስቴ አይዳ ሰለስቴ አይዳ የፍጥረት ንጋት የውብ ማለዳ ሰለስቴ አይዳ ሰለስቴ አይዳ አርጎ የሰራት መልከ ፀዐዳ ቤቷ ልዕልት ሆና ንጉስ የወለዳት ሎሌ አደረጏት እዛ በምርኮ ሲወስዷት ከአገር የወጣ ሰው ክብር የለውም ብላ ትንሽ መስላ ኖረች ሁሉን ተቀብላ ገራችው ሃይሉን ገራችው በፍቅር አስተማረችው ገብቷት የሷን መውደድ መርጦ እንደተሰዋ ከእሱ ጋር ጠጣችው መራራውን ጽዋ ታሪኩን በደሟ ጠቅሳ ልትጽፍበት ቆረጠች በፍቅሯ ሞቱን ልትሞትበት ሰለስቴ አይዳ ሰለስቴ አይዳ ህይወቷን ሰጠች ለፍቅር ብላ ሰለስቴ አይዳ ሰለስቴ አይዳ ተካፈለችው የነፍሱን እዳ ሰለስቴ አይዳ ሰለስቴ አይዳ ተካፈለችው የነፍሱን እዳ