Ney Wedene (Feat. Meek One)
Dibekulu
3:44በፍቅር አለም ካንቺ ጋራ ስቀርብሽ ደስታን ልጋራ መውደዴን ከቃሌ አትጠብቂው ሀቄን በአፍ ላታውቂው አንቺን ማፍቀሬን አልተርክም ስሜቴን በቃሌ አልሰብክም መርምረሽ እወቂው መውደዴን ተረድተሽ የሆዴን ሳስብሽ ለኩሼ ሻማ የፍቅሬን ፉጨት ሳሰማ ባይደርስም በየከተማው ግልፅ ነው የልቤ ዜማው ሳስብሽ ለኩሼ ሻማ የፍቅሬን ፉጨት ሳሰማ ባይደርስም በየከተማው ጥልቅ ነው የልቤ ዜማው ፍቅሬን ደግሼው እልቤ ላይ ሆኜልሽ ካላንቺ ማላይ ስጠራሽ ነይልኝ ከዳሴ ሳትጠብቂብኝ ውዳሴ ሀሳብሽ ብልሀት የበዛው መንፈስሽ ፍቅር የገዛው ፀባይሽ ሁሉን ያስማማ አክሱማዊት ነሽ አንቺማ ሳስብሽ ለኩሼ ሻማ የፍቅሬን ፉጨት ሳሰማ ባይደርስም በየከተማው ግልፅ ነው የልቤ ዜማው ሳስብሽ ለኩሼ ሻማ የፍቅሬን ፉጨት ሳሰማ ባይደርስም በየከተማው ጥልቅ ነው የልቤ ዜማው ፍቅራችን ለአመታት ኖሮ ዘመናትን አስቆጥሮ ይብቃልን ለብዙ ሻማ ትዝታን እንድንሻማው ፍቅራችን ለአመታት ኖሮ ዘመናትን አስቆጥሮ ይብቃልን ለብዙ ሻማ ትዝታን እንድንሻማው ይብቃልን ለብዙ ሻማ ትዝታን እንድንሻማው ይብቃልን ለብዙ ሻማ ትዝታን እንድንሻማው