Alkeserkum
Endale Woldegiorgis
6:25አንተን ፡ ሳስብ ፡ ጌታ ፡ አንተን ፡ ሳስብህ አንተን ፡ ሳስብ ፡ ገና ፡ አንተን ፡ ሳስብህ ወደ ፡ አምልኮ ፡ ባሕር ፡ ጠልቄ ፡ እሰጥማለሁ ወደ ፡ አንተ ፡ መገኛ ፡ አድራሻ ፡ እየገባሁ ስራዬ ፡ ስራዬ ፡ ማምለክ ፡ ነው በቅኔ ፡ አንተን ፡ መባረክ ፡ ነው ይሄው ፡ ጀመረኝ ፡ ለማመስገን ፡ በቅዱስ ፡ ስምህ ፡ መጉአደዱ እንዲህ ፡ ይበሉ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አንተን ፡ ለማምለክ ፡ የወደዱ (፪x) ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ ያለህ ፡ የምትኖር ፡ እግዚአብሔር ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ ያለህ ፡ የምትኖር ፡ እግዚአብሔር ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ ያለህ ፡ የምትኖር ፡ እግዚአብሔር ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ ያለህ ፡ የምትኖር ፡ እግዚአብሔር እንኳን ፡ እውነተኛ ፡ የሁሉም ፡ ባለቤት ፡ ሲከተል ፡ ልብ ፡ ያውቀው ሰው ፡ ያመልክ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ እስትንፋስ ፡ ከሌለው ፡ አምላክ ፡ አበጅቶ እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ለእኛም ፡ በራልን ፡ ሚለው ፡ ቃል ፡ ከገባኝ ለክብርህ ፡ ልዘምር ፡ ከጣኦታት ፡ መንደር ፡ ክንድህ ፡ ስላወጣኝ አንተን ፡ ሳመልክህ ፡ ደስታ ፡ ቢያደርገኝ ፡ እንደሰከረ ይሄ ፡ ጥቂት ፡ ነው ፡ ከዚህ ፡ ይብሳል ፡ እየጨመረ ጌታ ፡ ሳመልክ ፡ ደስታ ፡ ቢያደርገኝ ፡ እንደሰከረ ይሄ ፡ ጥቂት ፡ ነው ፡ ከዚህ ፡ ይብሳል ፡ እየጨመረ ይሄው ይሄው ይሄው ይሄው ፡ የአንተን ፡ ምሥጋና ፡ ጌታ ፡ ኢሄው ይሄው ይሄው ይሄው ይሄው ፡ የአንተን ፡ አምልኮ ፡ ጌታ ፡ ኢሄው የአንተን ፡ ምሥጋና ፡ ጌታ ፡ ኢሄው የአንተን ፡ አምልኮ ፡ ጌታ ፡ ኢሄው የአንተን ፡ ምሥጋና ፡ ጌታ ፡ ኢሄው የአንተን ፡ ዝማሬ ፡ ጌታ ፡ ኢሄው አንተን ፡ ሳስብ ፡ ከጭንቀት ፡ ጐጆ ፡ ስር ፡ ወጥቼ ፡ በማመስገን ፡ ክንፍ ፡ እበራለሁ አንተን ፡ ሳስብ ፡ ከፍ ፡ ያለብኝን ፡ በሙሉ ፡ ወደታች ፡ ማየት ፡ እጀምራለሁ አንተን ፡ ሳስብ ፡ ማጉረምረም ፡ ግቢ ፡ እኮ ፡ አይደለም ፡ ውሎ ፡ ማደሪያ ፡ ሰፈሬ አንተን ፡ ሳስብ ፡ ጌጠኛ ፡ ልብሴን ፡ ለብሼ ፡ ቅዱስ ፡ ነው ፡ ሚልህ ፡ መዝሙሬ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ ያለህ ፡ የምትኖር ፡ እግዚአብሔር ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ ያለህ ፡ የምትኖር ፡ እግዚአብሔር ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ ያለህ ፡ የምትኖር ፡ እግዚአብሔር ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ ያለህ ፡ የምትኖር ፡ እግዚአብሔር ነፍሥም ፡ አይቀርልኝ ፡ የአንተን ፡ ማንነት ፡ ክብርህን ፡ አስቤ ቅዱስ ፡ ሊል ፡ ይፈጥናል ፡ ታላቅነትህን ፡ ሊያመሰግን ፡ ልቤ የምሥጋና ፡ ሽቶ ፡ ሳልቆጥብ ፡ ሳልሰስት ፡ ለክብርህ ፡ ላፍሰው እንኳን ፡ ለደቂቃው ፡ ፳፬ ፡ ሰዓቱን ፡ ባመልክህ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው የሰራኸኝ ፡ የፈጠርከኝ ፡ ለዚህ ፡ ነውና ፈጽሞ ፡ አልጠግብም ፡ ዘምሬ ፡ አውርቼ ፡ የአንተን ፡ ምሥጋና የሰራኸኝ ፡ የፈጠርከኝ ፡ ለዚህ ፡ ነውና ፈጽሞ ፡ አልጠግብም ፡ ዘምሬ ፡ አውርቼ ፡ የአንተን ፡ ምሥጋና አንተን ፡ ሳስብ ፡ ከፍ ፡ ያለብኝን ፡ በሙሉ ፡ ወደታች ፡ ማየት ፡ እጀምራለሁ አንተን ፡ ሳስብ ፡ ማጉረምረም ፡ ግቢ ፡ እኮ ፡ አይደለም ፡ ውሎ ፡ ማደሪያ ፡ ሰፈሬ አንተን ፡ ሳስብ ፡ ጌጠኛ ፡ ልብሴን ፡ ለብሼ ፡ ቅዱስ ፡ ነው ፡ ሚልህ ፡ መዝሙሬ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ ያለህ ፡ የምትኖር ፡ እግዚአብሔር ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ ያለህ ፡ የምትኖር ፡ እግዚአብሔር ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ ያለህ ፡ የምትኖር ፡ እግዚአብሔር ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ ያለህ ፡ የምትኖር ፡ እግዚአብሔር