Yeaben
Ezira Hailemichel
4:17ባለ ድል ያረገን ስሙ ነው ባለ ድል ያረገን ክንዱ ነው ይሰራል በእኛ ላይ መንፈሱ ከፍ ይላል በዘመን ንጉሱ (2) ትከሻችን ጥሎ ቀንበር ሞገስ ተጭኖበት ክብር የመስቀሉን ኒሻን አርገን የደሙን ሀብል አጥልቀን በቀዩ ምንጣፍ ላይ በእምነት ተራምደን ገብተናል ገነት ድል ነስቶ ድል አልብሶናል ኢየሱስ ማዕረግ ሆኖናል ሊገለጥ ያለውን ክብር አይተነው በእምነት መነጽር ጨክነን እንሰብከዋለን ሁሉንም በአስቻለን ችለን አለን የከበረ መዝገብ ከነፍስ የምናምነዉ ከልብ መንፈሱ በእኛ ሲሰራ አዜምን በጦሩ ስፍራ ገልጦልን የእውቀቱን ሽታ በእምነት ካዘመተን ጌታ የለም ወደኋላ ማለት ሰባሪው ወጥቶልን ከፊት የምንሞት ስንመስል ህያው ፀጋው የበዛልን ደስታው አንዳችን የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ሆኗል ባርኮን