Teshenifeyalwe
Ezira Hailemichel
6:41ደግሞ ጎህ ሲቀድ ሲሆን ማለዳ ትውስ ይለኛል የፍቅርህ እዳ ልቤን ተጭኖት የአንተ ውለታ እፁብ እላለሁ ጠዋትም ማታ በአድማሱ ስፋት የማይሸፈን በጋራው ርዝመት የማይከደን አለኝ ትዝታ አለኝ ውለታ የተቀበልኩት በጎልጎታ ይህን ውለታ ይህን ስጦታ እስኪ ላስበው በእንባ ጠብታ ደግሞ ጎህ ሲቀድ ሲሆን ማለዳ ትውስ ይለኛል የፍቅርህ እዳ ልቤን ተጭኖት የአንተ ውለታ እፁብ እላለሁ ጠዋትም ማታ ጅራፍ ተቆጥሯል በሰውነትህ በብርቱ ገመድ ታስሯል እጅ እግርህ እንዲያ እየሆንክ ቻልክልኝ ጌታ በደምህ ነግቷል የነፍሴ ማታ ይህን ውለታ ይህን ስጦታ እስኪ ላስበው በእንባ ጠብታ ደግሞ ጎህ ሲቀድ ሲሆን ማለዳ ትውስ ይለኛል የፍቅርህ እዳ ልቤን ተጭኖት የአንተ ውለታ እፁብ እላለሁ ጠዋትም ማታ በማቃሰትህ አዜምኩኝ እኔ በፍቅርህ ቅኔ ሞልቶ ልሳኔ ያልረሳኸኝን እንዴት ረሳለሁ ዉዴን በእንባ አስታወሳለሁ ይህን ውለታ ይህን ስጦታ እስኪ ላስበው በእንባ ጠብታ ደግሞ ጎህ ሲቀድ ሲሆን ማለዳ ትውስ ይለኛል የፍቅርህ እዳ ልቤን ተጭኖት የአንተ ውለታ እፁብ እላለሁ ጠዋትም ማታ እድሜ ሲጎድል ሲያረጅ ዘመኑ በአንተ ላለ ግን አዲስ ነው ቀኑ እንደ ተሰቀልክ ሆነህ ከፊቴ ተስለህብኝ ፀንቷል እረፍቴ ይህን ውለታ ይህን ስጦታ እስኪ ላስበው በእንባ ጠብታ ደግሞ ጎህ ሲቀድ ሲሆን ማለዳ ትውስ ይለኛል የፍቅርህ እዳ ልቤን ተጭኖት የአንተ ውለታ እፁብ እላለሁ ጠዋትም ማታ