Munaye
Hewan Gebrewold
5:13ያምራል ያምራል ያምራል ልጁ ሁሉ በእጁ ነው በደጁ ያምራል ያምራል ያምራል ምቱ ዜማው ስልቱ የአውዳመቱ ዳማይ ልጅ ዳማይ ዳማይ የዛሬ አትውልም ወይ ስመኝህ ኖሬ እንዳው ስመኝ በአመት በአል አገጣጠመኝ ያለውም የሌለው በአቅሙ በደገሰው ያምራል ሲሰባሰብ ወዳጅ የከርሞ ሰው እጥፍ ድርብ ሀሴት ፍቅር የደስ ደስ ይደራል ይጎዝጎዝ ጠጅ ሳር እና አደስ እንኳንስ አንድ ላይ በስስት ላደገ ልዩ ቀን ነው ዛሬ እርቅ ለፈለገ እንኳን አደረሰን ለዚች ቀን በጤና አያጉድል አይለየን ለአመቱ እንደገና ያውዳመቱ ያውዳመቱ ያውዳመቱ ይሄ ነው ውበቱ ያገር ልጅ ያገር ልጅ ያገር ልጅ ነው የማር ጠጅ ዳማይ ልጅ ዳማይ ዳማይ የዛሬን አትውልም ወይ ስመኝህ ኖሬ እንዳው ስመኝ በአመት በአል አገጣጠመኝ ብርቅ የከንፈር ወዳጅ የሩቅ መስሎ እንግዳ ጠሪ አክባሪ እያለ ሲዘልቅ ወደ ጓዳ ከፍሪዳው በላይ ወይ ከዶሮው ፋንታ ፍቅርን ያደረጃል የአመት በአል ጨዋታ እንኳንስ አንድ ላይ በስስት ላደገ ልዩ ቀን ነው ዛሬ እርቅ ለፈለገ እንኳን አደረሰን ለዚች ቀን በጤና አያጉድል አይለየን ለአመቱ እንደገና ያውዳመቱ ያውዳመቱ ያውዳመቱ ይሄ ነው ውበቱ ያገር ልጅ ያገር ልጅ ያገር ልጅ ነው የማር ጠጅ ዳማይ ልጅ ዳማይ ዳማይ የዛሬ አትውልም ወይ ስመኝህ ኖሬ እንዳው ስመኝ በአመት በአል አገጣጠመኝ