Notice: file_put_contents(): Write of 645 bytes failed with errno=28 No space left on device in /www/wwwroot/muzbon.net/system/url_helper.php on line 265
Melat Kelemework - Tiz Yilegnal | Скачать MP3 бесплатно
Tiz Yilegnal

Tiz Yilegnal

Melat Kelemework

Альбом: Ende Maleda
Длительность: 5:58
Год: 2023
Скачать MP3

Текст песни

ትዝ ይለኛል ትዝ ትዝ
አይቼህ ስፈዝ አይተኸኝ ስትፈዝ
ወድሻለው ያልክኝ ለታ
እኔም ያልኩህ ለታ
የነበረን ደስታ
አንተ ብቻ ነበርክ ለኔ
እኔም ላንተ ብቻ
አናውቅ ለየብቻ
ህ... አ... ህ
አሁን በምን ለምን ውዴ
የኔም ያንተም ኑሮ
አይደል እንደ ድሮ
ሁ... ህ
አንተ ወዲህ አኔም ወዲያ
ከየት ሊውል ከየት ሊውል
ፍቅር ታዲያ
አንተ ወዲህ አኔም ወዲያ
ሆኖብናል ፍቅር እዳ
ድሮ ድሮማ ለሚያየን ሰው
ስናስቀና ይመኙት ነበር የኛን ፍቅር
ሲያዩን ገና
ምሳሌ አርገው የኛን ፍቅር ያስጨነቁን
እንዴት ነው የሚያምሩት ባሉ አፋቸው
እንዴትስ ያስታርቁን
ሁሉንም ረሰተን ብንዋደድ ይሻለናል
እመነኝ ሗላ ይሄስ ፍቅር ይቆጨናል
እኛው ካልፈታን የኛን ነገር
በራሳችን ባስታራቂማ ንፋስ ገባ መሃላችን
ይቅርታን ይዞት ይሉኝታን
ለፍቅር ስናጣ ቦታ
ያሁሉ ያ ሁሉ ደስታ
ሳናውቀው ሆነ ትዝታ
አንተ ወዲህ አኔም ወዲያ
ከየት ሊውል ፍቅር ታዲያ
አንተ ወዲህ አኔም ወዲያ
ሆኖብናል ፍቅር እዳ
ትዝ ይለኛል ትዝ ትዝ
አይቼህ ስፈዝ አይተኸኝ ስትፈዝ
ወድሻለው ያልክኝ ለታ
እኔም ያልኩህ ለታ
የነበረን ደስታ
አንተ ብቻ ነበርክ ለኔ
እኔም ላንተ ብቻ
አናውቅ ለየብቻ
ህ... አ... ህ
አሁን በምን ለምን ውዴ
የኔም ያንተም ኑሮ
አይደል እንደ ድሮ
ሁ... ህ
አንተ ወዲህ አኔም ወዲያ
ከየት ሊውል ፍቅር ታዲያ
አንተ ወዲህ አኔም ወዲያ
ሆኖብናል ፍቅር እዳ
አንተስ እንዴት ነህ ባለህበት ነህ ወይ ደና
እኔስ አልቻልኩም የኔ ፍቅር ከቻልክ ና
እውነት እውነቱን ከሆነማ ናፍቀኸኛል
አንተም ካልዋሸህ ይሄን ስሜት ይሰማሃል
አንዳንድ ጊዜማ በመሸነፍ ነው ማሸረፍ
ምን ኪሳራ አለው ተረትቼ አንተን ባተርፍ
ስንለያይ ግን ከተለይን እኛን ደስታ
ፍቅር ያሸንፍ እኛም ለሱ እንረታ
ይቅርታን ይዞት ይሉኝታ
ለፍቅር ስናጣ ቦታ
ያ ሁሉ ያ ሁሉ ደስታ
ሳናውቀው ሆነ ትዝታ
አንተ ወዲህ አኔም ወዲያ
ከየት ሊውል ፍቅር ታዲያ
አንተ ወዲህ አኔም ወዲያ
ሆኖብናል ፍቅር እዳ